እስራኤል ለሶማሊላንድ ሉዓላዊ ሀገርነት በይፋ እውቅና ሰጠች

ሰብስክራይብ

እስራኤል ለሶማሊላንድ ሉዓላዊ ሀገርነት በይፋ እውቅና ሰጠች

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ያሳለፉት ይህ ውሳኔ ቴላቪቭ ለምስራቅ አፍሪካዊቷ የሶማሊላንድ ግዛት እውቅና የሰጠች የመጀመሪያው ሀገር አድርጓታል፡፡

"ዓለም አቀፋዊ ሕጋዊነትን ለማግኘት ስናደርገው ለቆየነው የረጅም ጊዜ ጥረት ትልቅ ምዕራፍ ነው" ስትል ሶማሊላንድ ውሳኔውን አስመልክታ ባወጣችው መግለጫ አስታውቃለች።

ሶማሊላንድ ያገኘችው እውቅና በአፍሪካ ቀንድ ያላትን የተረጋጋ እና ዴሞክራሲያዊ ተዋናይነት እንዲሁም በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለውን የጋራ ፍላጎት የሚያንፀባርቅ መሆኑን አስታውቃለች።

እውቅናውን ተከትሎም ሶማሊላንድ የ "አብርሃም ስምምነት" ን ለመቀበል ያላትን ፍላጎት በመግለፅ፤ በመካከለኛው ምስራቅ እና በአፍሪካ ለሚደረገው ቀጣናዊ ትብብር፣ ውይይት እና ሰላም ቁርጠኝነቷን አመልክታለች።

መግለጫው አክሎም እውቅናው በሶማሊላንድ እና በእስራኤል መካከል ሙሉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመመስረት መንገድ የሚከፍት መሆኑንና በተለያዩ ዘርፎች ትብብርን ለማጠናከር እቅድ መኖሩን አረጋግጧል።

ℹ ሶማሊላንድ ከ1991 ጀምሮ የራሷ መንግሥት፣ የምርጫ ስርዓት እና ተቋማት ያሏት ራሷን የምታስተዳድር ግዛት ብትሆንም፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እውቅና ያልተሰጣት፤ በዓለም አቀፍ ደረጃም የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ አካል ተደርጋ ትቆጠራለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0