ቤኒን ከከሸፈው የመንቀለ መንግሥት ሙከራ በኋላ የፓርላማ ምርጫ ቅስቀሳ ጀመረች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱቤኒን ከከሸፈው የመንቀለ መንግሥት ሙከራ በኋላ የፓርላማ ምርጫ ቅስቀሳ ጀመረች
ቤኒን ከከሸፈው የመንቀለ መንግሥት ሙከራ በኋላ የፓርላማ ምርጫ ቅስቀሳ ጀመረች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.12.2025
ሰብስክራይብ

ቤኒን ከከሸፈው የመንቀለ መንግሥት ሙከራ በኋላ የፓርላማ ምርጫ ቅስቀሳ ጀመረች

የሀገሪቱ ብሔራዊ ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን በምርጫው የሚሳተፉ የአምስት ፖለቲካ ፓርቲዎችን ፍቃድ ማፅደቁን የአካባቢው የዜና ምንጭ ዘግቧል።

ቤኒን ጥር 3 ቀን 2018 ዓ.ም በምታካሂደው የፓርላማ እና የማዘጋጃ ቤት ምርጫ ሁለት የመንግሥት ደጋፊ ፓርቲዎች እና "ዘ ዴሞክራትስ" የተሰኘው ዋናው የተቃዋሚ ፓርቲ ለውድድር ይቀርባሉ።

ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ታሎን ከሁለት የሥልጣን ዘመን በኋላ መንበራቸውን የሚለቁ በመሆኑ መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም በሚካሄደው ምርጫ ሁለት የገዢው ፓርቲ እጩዎች ይፎካከራሉ።

የቤኒን ብሔራዊ ዘብ፤ በናይጄሪያ አየር ኃይል እና ኮትዲቯር በሚገኙ የፈረንሳይ ልዩ ኃይሎች በመታገዝ በሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን የታወጀውን ወታደራዊ የመንግሥት ግልበጣ ሙከራ ህዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም በአፋጣኝ ማክሸፉ ይታወሳል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0