የእንጦጦን የባሕር ዛፍ ደን በሀገር በቀል ዛፎች ለመተካት ጥናታዊ ጽሁፍ ቀረበ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየእንጦጦን የባሕር ዛፍ ደን በሀገር በቀል ዛፎች ለመተካት ጥናታዊ ጽሁፍ ቀረበ
የእንጦጦን የባሕር ዛፍ ደን በሀገር በቀል ዛፎች ለመተካት ጥናታዊ ጽሁፍ ቀረበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.12.2025
ሰብስክራይብ

የእንጦጦን የባሕር ዛፍ ደን በሀገር በቀል ዛፎች ለመተካት ጥናታዊ ጽሁፍ ቀረበ

ጥናታዊ ፅሁፉ ከአውስትራሊያ መጥተው የተተከሉትን የባሕር ዛፍ ዝርያዎች ከአካባቢዉ ሥነ-ምህዳርና ታሪካዊ ዳራ ጋር አስተሳስሮ በሌላ ሀገር በቀል ዛፎች መተካት እንዲቻል መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ቢሮ አስታውቋል፡፡

የምርምር ፅሁፉ ዛፎቹን በመተካት ሂደት ውስጥ ሊገጥሙ የሚችሉ ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ተግዳሮቶችን በመለየት ጥናት ላይ የተመሠረተ ዘላቂ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ያመላክታል ተብሏል፡፡

የባሕር ዛፍ ዝርያዎቹ እንዴት፣ መቼ እና በምን ሁኔታ እንደሚነሱ እንዲሁም በምን አይነት የሀገር በቀል ዛፍ ዝርያ መተካት እንዳለበቸው መለየት የጥናታዊ ፅሁፉ ትኩረት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ተጨማሪ ግብዓቶች ከተካተቱ በኋላ በቀጣይ የትግበራ ዕቅድ ይዘጋጃል ተብሏል፡፡

የባሕር ዛፍ ከአውስትራሊያ ወደ ኢትዮጵያ የገባው በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመን በ1886 ዓ.ም ነበር፡፡ በወቅቱ የኢትዮጵያ መልክዓ ምድር መራቆት በማሳየቱ በአማካሪያቸው ፈረንሳዊው ሞንዶን ቢዳሊን ጥቆማ ዛፉን አስመጥተው በእንጦጦ ጋራ ላይና በአካባቢው መትከላቸው ይነገራል፡፡

የባሕር ዛፍ ሥር የከርሰ ምድር ውኃ መጠንን እንደሚቀንስ፣ የአፈር ንጥረ ነገሮችን ለምነት እንደሚያሳጣ፣ በአካባቢው የሚገኙ ሰብሎችና እፅዋቶች በቂ የፀሐይ ብርሃን እንዳያገኙ እንደሚከለክል እና ምግብ በመሻማት በቂ ምርት በወቅቱ እንዳይሰጡ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳደር ይነገራል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0