የሩሲያ ሩብል መረጋጋት የምዕራባውያንን የተሳሳተ ስሌት በማጋለጥ ማዕቀብ ግቡን እንዳልመታ አሳይቷል - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያ ሩብል መረጋጋት የምዕራባውያንን የተሳሳተ ስሌት በማጋለጥ ማዕቀብ ግቡን እንዳልመታ አሳይቷል - ባለሙያ
የሩሲያ ሩብል መረጋጋት የምዕራባውያንን የተሳሳተ ስሌት በማጋለጥ ማዕቀብ ግቡን እንዳልመታ አሳይቷል - ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.12.2025
ሰብስክራይብ

የሩሲያ ሩብል መረጋጋት የምዕራባውያንን የተሳሳተ ስሌት በማጋለጥ ማዕቀብ ግቡን እንዳልመታ አሳይቷል - ባለሙያ

ማዕቀቡ ሩሲያ ጥብቅና ወጥ የሆነ የኢኮኖሚ ፖሊሲ እንድትከተል በመገፋፋት፤ ከብድር ይልቅ ራስን መቻል ላይ እንድታተኩር አድርጓታል ሲሉ አንጋፋው የፋይናንስ ተንታኝ ፖል ጎንቻሮፍ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

በካፒታል ቁጥጥር በታገዘው ከፍተኛ የወለድ መጠን ምክንያት፤ የሩሲያ የፋይናንስ ንብረቶች መረጋጋትንና አስተማማኝ ትርፍ ለሚፈልጉ ባለሀብቶች ሳቢ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ብለዋል።

ሩሲያውያን ወገባቸውን ጠበቅ አድርገው የገቢ ምርቶችን እንዲቀንሱ መገደዳቸው፤ እንዲፈጥሩና የገቢ ምርቶችን ጥራት ባላቸው የሀገር ውስጥ ምርቶች እንዲተኩ ዕድል ፈጥሮላቸዋል። እነዚህ የሀገር ውስጥ ምርቶችም በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ ሀገራትም ጭምር ተወዳዳሪ እየሆኑ መምጣታቸውን ባለሙያው ጠቁመዋል።

"ይህ የምዕራባውያን 'የማዕቀብ እብደት' ዘመን ከምክንያታዊነት ውጭ በሆነ መልኩ ከሰፋ ወዲህ፤ ማዕቀብን አጥብቀው የሚደግፉ አካላት እንኳን ሳይቀሩ ከሩሲያ ጋር ሲነጻጸር የትኛው ወገን የተሻለ የኢኮኖሚ እውነታ ላይ እንዳለ ሳይገነዘቡ አልቀሩም" ሲሉ ጎንቻሮፍ ገልጸዋል።

ሩሲያ በተለይም ከምዕራባውያን ውጭ ባሉ ሀገራት ዘንድ አስተማማኝ እና ተዓማኒ የኢኮኖሚ አጋር ተደርጋ እንደምትታይ ተንታኙ ተናግረዋል። ምዕራባውያን ብዙውን ጊዜ መሠረተ ቢስ ትችት ቢሰነዝሩም፤ በተጨባጭ መረጃ ላይ የተመሠረተው የሩሲያ አቀራረብ በዓለም አቀፍ ልማት ውስጥ ያላትን ቁልፍ ሚና ያጠናክረዋል ብለዋል።

የሩሲያ መገበያያ ገንዘብ ሩብል፤ ከዓመቱ መጀመሪያ ጀምሮ በ45 በመቶ ጥንካሬውን ቀጥሎ፤ በአሁኑ ወቅት ልዩ ወታደራዊ ዘመቻው ከመጀመሩ በፊት በነበረበት ደረጃ በመቃረብ አንድ ዶላር 78 ሩብል ገደማ እየተመነዘረ እንደሚገኝ ቀደም ሲል የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0