ከኢትዮጵያ አየር ኃይል የመጀመሪዎቹ አብራሪዎች አንዱ የሆኑት ሻለቃ ሚሻካ ባብቼቭ እና ሌሎች ጀግኖችን የሚዘክር ሐውልት ሊመረቅ ነው

ሰብስክራይብ

ከኢትዮጵያ አየር ኃይል የመጀመሪዎቹ አብራሪዎች አንዱ የሆኑት ሻለቃ ሚሻካ ባብቼቭ እና ሌሎች ጀግኖችን የሚዘክር ሐውልት ሊመረቅ ነው

ሐውልቱ በአባታቸው ሩሲያዊ ለሆኑት ሻለቃ ሚሽካ ባብቼቭ እንዲሁም ለሌሎች ጀግኖች መታሰቢያነት የሚቆም መሆኑን በኢትዮጵያ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለከባድ ጥገና ማዕከል ኃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል መሰረት ጌታቸው ከስፑትኒክ አፍሪካ ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

"ሻለቃ ሚሽካ ባብቼቭን ጨምሮ በኢትዮጵያ አየር ኃይል ደማቅ ታሪክ የፃፉ ብዙ ጀግኖች አሉ። አዲስ ጀግኖችን ለማፍራት እነዚህን ባለውለታዎች ማክበር ስለሚገባ ሁሉንም የሚወክል ሐውልት ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ ነን" ብለዋል።

ኃላፊው ሐውልቱ የፊታችን እሑድ እንደሚመረቅም ገልጸዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0