#viral | ተቃዋሚዎች በአልባኒያ ፓርላማ ርችት የታከለበት አመፅ ቀሰቀሱ

ሰብስክራይብ

#viral | ተቃዋሚዎች በአልባኒያ ፓርላማ ርችት የታከለበት አመፅ ቀሰቀሱ

አዲሱ የአልባኒያ የሰብዓዊ መብት እንባ ጠባቂ የቃለ መሃላ ሥነ-ሥርዓት በሚከናወንበት ወቅት፤ በርካታ መቀመጫ የያዘው የተቃዋሚው የዲሞክራቲክ ፓርቲ አባላት ምክር ቤቱን ወደ ትርምስ ቀይረውታል። የፓርላማ አባላቱ ደማቅ ተቀጣጣይ ርችት በመለኮስ፣ የውሃ ጠርሙሶችንና ወረቀቶችን በመወርወር፣ የፀጥታ ጠባቂዎችን በመግፋት እና የመንግሥት መቀመጫዎችን ለአጭር ጊዜ በመያዝ ስብሰባው እንዲቋረጥ አድርገዋል።

በዚህም ገዥው የሶሻሊስት ፓርቲ በድርጊቱ ውስጥ ተሳትፈዋል ተብለው የተከሰሱ 29 የፓርላማ አባላት እንዲታገዱ ጠይቋል።

🪧 በፓርላማው ውስጥ የተቀሰቀሰው ትርምስ በፍጥነት ወደ ጎዳናዎች ተዛምቷል። በቲራና በተቀሰቀሰው መጠነ ሰፊ ተቃውሞ፤ ሰልፈኞች ጠቅላይ ሚኒስትር ኤዲ ራማ ሥልጣን እንዲለቁ እና የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤሊንዳ ባሉኩ የፓርላማ ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ እየጠየቁ ይገኛሉ። አንዳንድ ሰልፎች ወደ አመጽ እንደተቀየሩ እና ሞሎቶቭ ኮክቴል (የፈንጂ ጠርሙስ) ስለመወርወሩም ተዘግቧል።

አለመረጋጋቱ ገዥው የሶሻሊስት ፓርቲ ጠንካራ ሥልጣን አለው በሚባልበት ወቅት የመጣ ነው። ባሳለፍነው ግንቦት 11 በተካሄደ ምርጫ ፓርቲው 52 በመቶ ድምፅ በማግኘት ከፓርላማው 140 መቀመጫዎች ውስጥ 83ቱን ማሸነፍ ችሏል። ተቃዋሚው የዲሞክራቲክ ፓርቲ 50 መቀመጫዎችን አግኝቷል።

ፖለቲካዊ ቀውሱ አልባኒያ ከሰሜን ጎረቤቷ ሞንቴኔግሮ ጋር ከምዕራብ ባልካን ሀገራት መካከል የአውሮፓ ኅብረት አባል ለመሆን ግንባር ቀደም ተመራጭ ሆና በምትታይበት ወቅት የመጣ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
#viral | ተቃዋሚዎች በአልባኒያ ፓርላማ ርችት የታከለበት አመፅ ቀሰቀሱ - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
#viral | ተቃዋሚዎች በአልባኒያ ፓርላማ ርችት የታከለበት አመፅ ቀሰቀሱ - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0