- Sputnik አፍሪካ, 1920
Sovereignty Sources
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ደቡብ አፍሪካን በቀጣዩ የቡድን 20 ጉባዔ ለሞን አንጋብዝም አሉ? ፖለቲካ መር ወይስ የህግ መሠረት ያለው ጉዳይ?

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ደቡብ አፍሪካን በቀጣዩ የቡድን 20 ጉባዔ ለሞን አንጋብዝም አሉ? ፖለቲካ መር ወይስ የህግ መሠረት ያለው ጉዳይ?
ሰብስክራይብ

''ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቀጣይ በሀገራቸው በሚካሄደው የቡድን 20 ሀገራት ጉባዔ ደቡብ አፍሪካን እንደማይጋብዙ መናገራቸው ወደፊት የቡድኑን አቃፊነትና ተቀባይነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው - የፕሬዝዳንቱ ንግግርን ተከትሎ በርካታ ሀገራት አጋርነታቸውን ለደቡብ አፍሪካ አሳይተዋል '' ሲሉ በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል መምህሩ ጃራ ሳሙኤል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው ፕሮግራሙ በክፍል አንድ፣ በቅርቡ በደቡብ አፍሪካ የተደረገውን የቡድን 20 ሀገራት ጉባዔን ተከትሎ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቀጣዩ ጉባዔ ደቡብ አፍሪካን እንደማይጋብዙ መናገራቸውን በተመለከተ ከዓለም አቀፍ ህግና የሞራል መመዘኛዎች አኳያ በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል መምህሩ ጃራ ሳሙኤል ጋር ቆይታን አድርገናል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው የመንገድ ትሪፊክ አደጋ በተመለከተ በአውቶሞቲቭ ሙያ የረጅም ዓመት ልምድ ያላቸው ፋሲል አስራት ጋር ተወያይተናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ
Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0