ግብፅ በኤርትራ እና ጅቡቲ የሚገኙ ስትራቴጂካዊ ወደቦችን ለማልማት መስማማቷ ተሠማ

ግብፅ በኤርትራ እና ጅቡቲ የሚገኙ ስትራቴጂካዊ ወደቦችን ለማልማት መስማማቷ ተሠማ
የኤርትራውን አሰብ እና በጅቡቲ የሚገኘውን የዶራሌህ ወደብ ለማልማትና ለማዘመን ከሀገራቱ ጋር ከመጋረጃ ጀርባ ስምምነት ላይ መድረሷን "ዘ ናሽናል" የተሰኘው የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጋዜጣ የካይሮ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።
🪖 ይህ ስምምነት ግብፅ በስትራቴጂካዊው የባብ አል-መንደብ ሰርጥ አቅራቢያ ወታደራዊ እና የባሕር ኃይል ይዞታዋን እንድታጠናክር የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡
ስምምነቱ የግብፅ የጦር መርከቦች በወደቦቹ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል እና የተወሰኑ የግብፅ ወታደራዊ አባላት የሚሠማሩባቸው ተቋማት መገንባትንም ያካትታል ተብሏል።
የካይሮ እርምጃ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በተፋጠጠቻት ኢትዮጵያ ላይ ጫና የመፍጠር ዓላማ እንዳለው ዘገባዎች አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ ግድቡን የአፍሪካን ራስን የመቻል እና እድገት የተላበሰ ስትል በቅርቡ ባወጣቸው መግለጫ ገልጻዋለች፡፡ ሀገሪቱ የወቅቱን እና የመጪውን ትውልድ ፍላጎት ለማሟላት በአባይ ወንዝ የመጠቀም መብት እንዳላትም አስረግጣለች፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ፤ "ኢትዮጵያ የአሰብ ወደብን በዘላቂነት እና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ለማግኘት አማራጭ መንገዶችን ለመመልከት ዝግጁ" እንደሆነች መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X