በኢትዮጵያ የተመረቱ የማዕድን ማቀነባበሪያ ማሽኖች ወደ ሥራ ሊገቡ መሆኑ ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበኢትዮጵያ የተመረቱ የማዕድን ማቀነባበሪያ ማሽኖች ወደ ሥራ ሊገቡ መሆኑ ተገለፀ
በኢትዮጵያ የተመረቱ የማዕድን ማቀነባበሪያ ማሽኖች ወደ ሥራ ሊገቡ መሆኑ ተገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.12.2025
ሰብስክራይብ

በኢትዮጵያ የተመረቱ የማዕድን ማቀነባበሪያ ማሽኖች ወደ ሥራ ሊገቡ መሆኑ ተገለፀ

በሀገር ውስጥ የተመረቱት የማዕድን መቁረጫ፣ የማለስለሻና የቅርጽ ማውጫ ማሽኖች በቅርቡ ወደ አገልግሎት እንደሚገቡ የማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

ኢንስቲትዩቱ ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀት ያመረታቸው ማሽኖች የጌጣጌጥ ማዕድናት ላይ እሴት ጨምሮ በማምረት የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ እንደሚያስችሉ ተመላክቷል፡፡

ዘርፉን በዘመናዊ ስርዓት ለመምራት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግንባታ እየተከናወነ እንደሆነ እና የማዕድን ማውጫ አደጋን የሚከላከል የደህንነት ምሰሶ ዲዛይን እና የኢትዮጵያ የጌጣጌጥ ማዕድናት ልማት ፍኖተ ካርታ ዝግጅት በመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0