ዓለም አቀፉ የገና በዓል የጥፋት ውሃ መዘግየቱን ጋናዊው 'ነቢይ' ገለፀ
15:02 25.12.2025 (የተሻሻለ: 15:04 25.12.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዓለም አቀፉ የገና በዓል የጥፋት ውሃ መዘግየቱን ጋናዊው 'ነቢይ' ገለፀ
'አምላክ' ብዙ ሰዎችን ማስተናገድ እንዲቻል ተጨማሪ መርከቦች እንዲገነቡ ሲል የጥፋት ውሃው እንዲዘገይ ማድረጉን ኢቦ ኖህ የተባለው ግለሰብ ተናግሯል።
ይህ "ነቢይ ነኝ" ሲል ራሱን የሚጠራው ግለሰብ ባለፈው ነሐሴ ወር መጨረሻ በዩቲዩብ ባሰራጨው ቪዲዮ፤ አምላክ በአውሮፕውያኑ ታህሳስ 25፣ በገና ዕለት ከፍተኛ ዝናብ እንደሚዘንብ እንዳስጠነቀቀውና ሰዎችን ለማዳን መርከብ እንዲሠራ እንዳዘዘው ገልጾ ነበር። በኋላ ላይ ደግሞ 10 መርከቦች እንደሚኖሩ ተናግሯል።
"ነቢዩ" ሰዎች በገና ዋዜማ ወደ መርከቦቹ ከመሮጥ ይልቅ ቤታቸው ሆነው በዓሉን እንዲያከብሩ አሳስቧል። አክሎም የጥፋት ውሃው "በመዘግየቱ" ምክንያት ለመርከቡ ትኬት እንደማይሸጥ ወይም ፍላጎት ካላቸው ሰዎች ገንዘብ እንደማይቀበል ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X