ኢትዮጵያ በሠለጠኑ ውሾች አማካኝነት የዱር እንስሳት ዝውውር ቁጥጥርን ማጠናከሯ ተገለፀ
14:22 25.12.2025 (የተሻሻለ: 14:24 25.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በሠለጠኑ ውሾች አማካኝነት የዱር እንስሳት ዝውውር ቁጥጥርን ማጠናከሯ ተገለፀ
አነፍናፊ ውሾቹ የዱር እንስሳት ዝውውርን ከመከላከል ባሻገር የተለያዩ የወንጀል ድርጊቶችን ለመለየት አቅም መፍጠራቸውን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኩመራ ዋቅጅራ ተናግረዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ ይህን ያሉት በዱር እንስሳት ላይ የሚፈጸመውን ሕገ-ወጥ ዝውውር የመለየት እና የመቆጣጠር አቅምን ለማሳደግ ያለመ የሦስት ቀን የሥልጠና መርሃ ግብር በአዲስ አበባ መካሄድ በጀመረበት ወቅት ነው።
የአፍሪካ የዱር እንስሳት ፋውንዴሽን የፕሮግራም አስተባባሪ ገበያው ድልነሳ በበኩላቸው፤ “ሥልጠናው ሀገራዊ የሕግ ማስከበር አቅምን ለማሳደግ እና ውሾቹ የሚያገኟቸው ማስረጃዎች በፍርድ ቤት የሚቀርቡበትን ዕድል ለማሻሻል ያለመ ነው” ብለዋል።
ኢትዮጵያ ካለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ጀምሮ በአፍሪካ የዱር እንስሳት ፋውንዴሽን የሠለጠኑ አራት አነፍናፊ ውሾችን እና አሰተባባሪዎችን በያዘ የጥበቃ ቡድን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የዱር እንስሳት ሕገ-ወጥ ዝውውርን ስትከላከል ቆይታለች፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X