በኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ላይ የ38 አፍሪካ ሀገራት የአየር ኃልል አዛዦች እንደሚታደሙ ተገለፀ
11:30 25.12.2025 (የተሻሻለ: 11:44 25.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ላይ የ38 አፍሪካ ሀገራት የአየር ኃልል አዛዦች እንደሚታደሙ ተገለፀ
ከጥር 15 እስከ 19፣ 2018 ዓ.ም በሚቆየው ዝግጅት፤ "የኢትዮጵያ አየር ኃይል የነጻነት እና የአንድነት ምልክት" በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ የሩሲያ፣ የዩናይትድ አረብ ኤሚሬቶች፣ የሞሮኮ እና የቼክ ሪፐብሊክ አየር ኃይሎች የአየር ትርዒት እንደሚያሳዩ፤ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የ1ኛ አየር ምድብ አዛዥ ብርጋድየር ጀነራል ቡሩክ ሰይፉ ገልጸዋል፡፡
እንደ የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘገባ፤ የሩሲያ አየር ኃይል ከ100 በላይ የልዑካን ቡድን አባላትን ያካትታል፡፡
የሩሲያ እና የቻይናን ጨምሮ 28 የአቪዬሽን ኩባንያዎች በዓሉን አስመልክቶ በሚዘጋጀው የአቪዬሽን ኤክስፖ ላይ ምርቶቻቸውን ለእይታ እንደሚያቀርቡም ተመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X