ታሪካዊው የአልጄሪያ የቅኝ አገዛዝ ሕግ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም መነሳሳት የሚፈጥር ነው - አልጄሪያዊ ተንታኝ
10:00 25.12.2025 (የተሻሻለ: 10:04 25.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ታሪካዊው የአልጄሪያ የቅኝ አገዛዝ ሕግ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም መነሳሳት የሚፈጥር ነው - አልጄሪያዊ ተንታኝ
"የዚህ ሕግ መጽደቅ የአፍሪካ ሀገራትን ለማነሳሳት ምክንያት ይሆናል። በተመሳሳይ የቅኝ አገዛዝን በወንጀልነት የሚፈርጁ ሕጎችን በማጽደቅ ጥምረት መፍጠር ይችላሉ" ሲሉ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያው ፋሪድ ቤንያያ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
አስተያየቱ የአልጄሪያ ፓርላማ የፈረንሳይ ቅኝ አገዛዝን ወንጀል የሚያደርግ አዲስ ሕግ ማክሰኞ በሙሉ ድምፅ ካፀደቀ በኋላ የመጣ ነው። ሕጉ እ.አ.አ ከ1830 እስከ 1962 የቆየውን የፈረንሳይ ቅኝ አገዛዝ በይፋ "መንግሥታዊ ወንጀል" ሲል ፈርጆታል።
ፈረንሳይ ለአልጄሪያ እና ለመላው የአፍሪካ አኅጉር በቅኝ ግዛት ወቅት ለፈፀመቻቸው ወንጀሎች ካሳ መክፈል አለባት ያሉት ቤንያያ፤ "በማሊ፣ በኒጀር፣ በቻድ፣ በሴኔጋል እና በሌሎች ሀገራት የተፈጸሙ የጅምላ ግድያዎችን" ጠቅሰዋል።
ከ1830 እስከ 1962፤ 5 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች መገደላቸውን በመጥቀስ፤ የፈረንሳይ ቅኝ አገዛዝ ለ "ብዙ ስቃይ" እና ለዘመናት የብሔራዊ ሀብቶች ዘረፋ ምክንያት ነበር ብለዋል።
"ለዚህ ነው ፈረንሳይ እውቅና ለመስጠት አሻፈረኝ የምትለው" ሲሉ ደምድመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X