የውጭ ኃይሎች በቤኒን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ውስጥ ተሳትፈዋል - ፕሬዝዳንት ታሎን

ሰብስክራይብ

የውጭ ኃይሎች በቤኒን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ውስጥ ተሳትፈዋል - ፕሬዝዳንት ታሎን

“ጥቃቱ የተፈጸመው ሥልጣን መልሰው ለማግኘት በሚፈልጉ የተገለሉ ዓላማ ቢስ ግለሰቦች የተጠመዘዙ ጥቂት የሀገሬ ልጆች እንዲሁም በተወሰኑ የውጭ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ባለሥልጣናት ነው” ሲሉ የቤኒን መሪ በትናንትናው ዕለት ለሀገሪቱ ሕዝብ ባደረጉት ንግግር አስታውቀዋል።

ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ታሎን ስለእነዚህ ግለሰቦች ምንም ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም።

ህዳር 28 ቀን የጦር መኮንኖች ቡድን በብሔራዊ ቴሌቪዥን ቀርበው ሥልጣን መጨበጣቸውን እና ፕሬዚዳንቱን ከሥልጣን እንዳወረዱ ማስታወቃቸው ይታወሳል።

በናይጄሪያ አየር ኃይል እና በኮትዲቯር በተሠማሩ የፈረንሳይ ልዩ ኃይሎች ድጋፍ የተደረገላቸው ለሪፐብሊኩ ታማኝ የሆኑ የብሔራዊ ዘብ ክፍሎች የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን በፍጥነት ማክሸፍ ችለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0