- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል።አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

የአውሮፓ የከሸፈው ቁማር እና የሩሲያ ድል ፡- በፑቲን ወሳኙ ዓመታዊ ንግግር

የአውሮፓ የከሸፈው ቁማር እና የሩሲያ ድል ፡- በፑቲን ወሳኙ ዓመታዊ ንግግር
ሰብስክራይብ

“ፕሬዝዳንት ፑቲን አሁን ኢኮኖሚውን በማረጋጋት እና ተጨባጭ እድገት ወደሚታይበት ደረጃ ማድረስ ችለዋል … ዛሬ በሩሲያ እያየን ያለነው የኢኮኖሚ ለውጥ ብቻ ሳይሆን፣ የፑቲንን አመራር ተጽእኖ ፈጣሪነት ነው” ሲሉ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪው ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

አዉሮፓዉያን ዛሬም በከሸፈ የቁማር መንገዳቸው ቢቀጥሉም የሩስያ ገናና ድል ግን ቀጥሏል።

”አውሮፓውያን በውጭ አገራት የተቀመጡ የሩሲያን ንብረት እና ገንዘብ በመውሰድ ለዩክሬን ለመስጠት ማሰባቸው የደቡቡ ዓለም ከአውሮፓውያን ጋር የሚኖረውን አሰራር እንዲያጤን ቀጥተኛ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው” ያሉት ደግሞ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩቨርሲቲ የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ አንዳለ ንጉሴ ናቸው።

በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የዓመቱ ማጠቃለያ መግለጫ ወቅት ያነሷቸዉን ጉዳዮች መነሻ በማድረግ ከዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ እና ከደቡብ ለደቡብ ትብብር አንፃር የሚኖራቸዉን አንድምታዎች እንቃኛለን። ለዚህም ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪዉን ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩቨርሲቲ የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩን አንዳለ ንጉሴን አነጋግረናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerAfripods Spotify Pocket Casts Podcast Addict CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0