ኢትዮጵያ በአፍሪካ በታዳሽ ኃይል ለሚሠሩ የዳታ ማዕከላት ስትራቴጂካዊ ማዕከል እየሆነች መምጣቷ ተገለጸ
17:12 24.12.2025 (የተሻሻለ: 17:14 24.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በአፍሪካ በታዳሽ ኃይል ለሚሠሩ የዳታ ማዕከላት ስትራቴጂካዊ ማዕከል እየሆነች መምጣቷ ተገለጸ
የኢትዮጵያ ሰፊ የታዳሽ ኃይል አቅም ስትራቴጂካዊ ብልጫ እንዲኖራት ማድረጉን አፍሪካ ቢዝነስ መፅሄት በሠራው ትንታኔ አስነብቧል።
በአኅጉሪቱ አምስት ግዙፍ ገበያዎች ውስጥ የዳታ ማዕከል ፍላጎት እ.ኤ.አ 2030 በአምስት እጥፍ ያድጋል ተብሎ የሚገመት ሲሆን ኢትዮጵያም የዚህ ዕድገት ዋነኛ ማዕከል እንደምትሆን ይጠበቃል፡፡
የኢትዮጵያ የኃይል ምንጭ በዋናነት በውሃ ኃይል ላይ የተመሠረተ መሆኑ የአካባቢ ጥበቃን ያገናዘቡ "አረንጓዴ የዳታ ማዕከላትን" ለመገንባት አማራጭ መዳረሻ እንደሚያደርጋትም ተመላክቷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X