የአልጄሪያ ፓርላማ የፈረንሳይን ቅኝ አገዛዝ በወንጀልነት የሚፈርጅ ሕግ በሙሉ ድምጽ አፀደቀ
17:03 24.12.2025 (የተሻሻለ: 17:44 24.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአልጄሪያ ፓርላማ የፈረንሳይን ቅኝ አገዛዝ በወንጀልነት የሚፈርጅ ሕግ በሙሉ ድምጽ አፀደቀ
ስለ ሰነዱ ቁልፍ ዝርዝሮች፦
🟠 የፀደቀው ሕግ 5 ምዕራፎችና 27 አንቀጾች አሉት።
🟠 ሕግ በማግኘት መብት እና ታሪካዊ ፍትሕን በሚያረጋግጡ እንዲሁም ከተጠያቂነት ማምለጥን ውድቅ በሚያደርጉ ዓለም አቀፍ የሕግ መርሆዎች ላይ የተመሠረተ ነው።
🟠 የፈረንሳይን ቅኝ አገዛዝ ወንጀሎች በመዘረዝር፤ ፈረንሳይ በአልጄሪያ የቅኝ አገዝዛ ታሪኳ ምክንያት ተጠያቂ መሆን እንዳለባት ያሰቀምጣል።
🟠 ፈረንሳይ ለፈጸመችው ወንጀል እውቅና እንድትሰጥ እና ይቅርታ እንድትጠይቅ አሠራሮችን ያቋቁማል።
🟠 ቅኝ አገዛዝን ማሞገስ ወይም ማስተዋወቅን እንደ ወንጀል የሚቆጥሩ የቅጣት እርምጃዎችን አካቷል።
🟠 እነዚህን ተጠያቂነቶች ለታሪካዊ እርቅና ለብሔራዊ መታሰቢያ ጥበቃ መሠረት ናቸው ሲል ይገልጻቸዋል።
"[የፈረንሳይን ቅኝ አገዛዝ በመወንጀልነት መፈረጅ] በአልጄሪያ እና በመላው ዓለም ጠላቶች ላይ የተቃጣ የፓርላማ ምላሽ ነው" ሲሉ የብሔራዊ ታሪክ እና መታሰቢያ ኮሚቴ አስተባባሪ መሐመድ ላህሰን ዜጊዲ በፓርላማ ስብሰባ መክፈቻ ላይ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X