“ሊወደስ የሚገባው እድገት አስመዝግበናል” ፦ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት የሀገሪቱን የ2025 ዕድገትና ዓለም አቀፍ አመራር አወደሱ

ሰብስክራይብ

“ሊወደስ የሚገባው እድገት አስመዝግበናል” ፦ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት የሀገሪቱን የ2025 ዕድገትና ዓለም አቀፍ አመራር አወደሱ

ፖል ማሻቲሌ ለደቡብ አፍሪካውያን መልካም የገና እና የአዲስ ዓመት በዓል ምኞታቸውን ገልጸው፤ ከቀናቶች በኋላ የሚጠናቀቀው 2025 ሊወደስ የሚገባው መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። የሀገሪቱን ጽናት፣ አንድነትና ዕድገት በማንሳት፤ 0.5 በመቶ የጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት፣ ከስታንዳርድ ኤንድ ፑርስ የተገኘው የመበደር አቅም ደረጃ ማሻሻያ እና የኃይል ቀውሱን በመቆጣጠር የታየውን መሻሻል እና ሌሎች ቁልፍ ስኬቶችን ጠቅሰዋል።

ምክትል ፕሬዚዳንቱ የደቡብ አፍሪካ የቡድን 20 አመራርነት ዓለም አቀፍ አጋርነቶችን በማጠናከር እና ለደቡባዊው ዓለም ድምጽ ከመሆን ረገድ ስኬታማ እንደነበር አስታውሰዋል።

በኅዳር ወር ብሔራዊ አደጋ ተብሎ የታወጀውን በፆታ ላይ የተመሠረተ ጥቃትና የሴቶች ግድያን ለመቅረፍ የተወሰዱትን ወሳኝ እርምጃዎች በማድነቅ ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

"የገጠመንን እያንዳንዱን ፈተና በመቋቁም እና ባስመዘገብነው እያንዳንዱ ድል፤ የማንነታችን መገለጫ የሆነውን የኡቡንቱ መንፈስ አሳይተናል።"

ሙሉ ንግግራቸውን ከቪዲዮው ይመልከቱ

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0