https://amh.sputniknews.africa/20251224/2649667.html
ኦፓል መሰል ማዕድናት ወደ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ እንዲገቡ መደረጉ ሕገ-ወጥ ንግድን በማስቀረት፤ ለአምራቾች ፍትሐዊ ዋጋ ያረጋግጣል - የዘርፉ ባለሙያ
ኦፓል መሰል ማዕድናት ወደ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ እንዲገቡ መደረጉ ሕገ-ወጥ ንግድን በማስቀረት፤ ለአምራቾች ፍትሐዊ ዋጋ ያረጋግጣል - የዘርፉ ባለሙያ
Sputnik አፍሪካ
ኦፓል መሰል ማዕድናት ወደ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ እንዲገቡ መደረጉ ሕገ-ወጥ ንግድን በማስቀረት፤ ለአምራቾች ፍትሐዊ ዋጋ ያረጋግጣል - የዘርፉ ባለሙያ እርምጫው ደላሎችን እና የኮንትሮባንድ ዝውውርን የሚስቀር ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ መደበኛ... 24.12.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-12-24T15:55+0300
2025-12-24T15:55+0300
2025-12-24T16:04+0300
sputnik africa
telegram sputnik_ethiopia
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07e9/0c/18/2649513_0:42:800:492_1920x0_80_0_0_8b84877c00e1a93f3c31e374f326534c.jpg
ኦፓል መሰል ማዕድናት ወደ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ እንዲገቡ መደረጉ ሕገ-ወጥ ንግድን በማስቀረት፤ ለአምራቾች ፍትሐዊ ዋጋ ያረጋግጣል - የዘርፉ ባለሙያ እርምጫው ደላሎችን እና የኮንትሮባንድ ዝውውርን የሚስቀር ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ መደበኛ የኦፓል ግብይት ሊያስጀምር እንደሆነ መግለጹን አስመልክቶ ለስፑትኒክ አፍሪካ አሰትያየታቸውን የሰጡት የማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬከተር ብስራት ከበደ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ “መደበኛ የዋጋ አወሳሰን ስርዓቶችን መዘርጋት፣ አምራቾች መደበኛ ባልሆኑ ደላሎች ላይ ያላቸውን ጥገኝነት ይቀንሳል። ግብይቶችን በዲጂታል ዘዴ በመከታተል፣ የኮንትሮባንድ ዝውውርን በቀላሉ መለየት ያስችላል። በተጨማሪም የኦፓል አምራቾች ፍቃድ ካላቸው ላኪዎች ጋር በቀጥታ በመገናኘት እና ተወዳዳሪ የዋጋ ጨረታዎችን በማግኘት፣ ከዓለም አቀፍ የገበያ ደረጃዎች ጋር የተጣጣመ ፍትሐዊ ዋጋ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።”ኢትዮጵያ ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት የዘለለ ራዕይ አንግባ ያለቁ የከበሩ ድንጋዮች አቅራቢ የመሆን የረጅም ግዜ ዕቅድ እንዳላትም ባለሙያው ገልፀዋል፡፡ “እንደ ስልታዊ ዕቅድ የተያዘው እሴት ለተጨመረባቸው የወጪ ንግዶች ማበረታቻ መስጠት ነው፡፡...ለጊዜው ኢትዮጵያ የገበያ ተደራሽነትን በማረጋገጥ እና የሀገር ውስጥ የማቀነባበር አቅምን እያሳደገች፤ ጥሬ እና ያለቁ ኦፓሎችን ለመገበያየት የኢትዮጵያ ምርት ገበያን ትጠቀማለች። የረጅም ጊዜ ራዕዩ ኢትዮጵያን ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወደ ያለቁ የከበሩ ድንጋዮች አምራችነት በማሸጋገር፤ በብሪክስ እና በዓለም አቀፍ ገበያዎች ውስጥ ተወዳዳሪ ሆና እንድትገኝ ማድረግ ነው።”በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
2025
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/img/07e9/0c/18/2649513_45:0:756:533_1920x0_80_0_0_64bc826a751affbd272d7b0881422949.jpgSputnik አፍሪካ
feedback.africa@sputniknews.com
+74956456601
MIA "Rossiya Segodnya"
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
sputnik africa, telegram sputnik_ethiopia
ኦፓል መሰል ማዕድናት ወደ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ እንዲገቡ መደረጉ ሕገ-ወጥ ንግድን በማስቀረት፤ ለአምራቾች ፍትሐዊ ዋጋ ያረጋግጣል - የዘርፉ ባለሙያ
15:55 24.12.2025 (የተሻሻለ: 16:04 24.12.2025) ኦፓል መሰል ማዕድናት ወደ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ እንዲገቡ መደረጉ ሕገ-ወጥ ንግድን በማስቀረት፤ ለአምራቾች ፍትሐዊ ዋጋ ያረጋግጣል - የዘርፉ ባለሙያ
እርምጫው ደላሎችን እና የኮንትሮባንድ ዝውውርን የሚስቀር ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ መደበኛ የኦፓል ግብይት ሊያስጀምር እንደሆነ መግለጹን አስመልክቶ ለስፑትኒክ አፍሪካ አሰትያየታቸውን የሰጡት የማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬከተር ብስራት ከበደ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
“መደበኛ የዋጋ አወሳሰን ስርዓቶችን መዘርጋት፣ አምራቾች መደበኛ ባልሆኑ ደላሎች ላይ ያላቸውን ጥገኝነት ይቀንሳል። ግብይቶችን በዲጂታል ዘዴ በመከታተል፣ የኮንትሮባንድ ዝውውርን በቀላሉ መለየት ያስችላል። በተጨማሪም የኦፓል አምራቾች ፍቃድ ካላቸው ላኪዎች ጋር በቀጥታ በመገናኘት እና ተወዳዳሪ የዋጋ ጨረታዎችን በማግኘት፣ ከዓለም አቀፍ የገበያ ደረጃዎች ጋር የተጣጣመ ፍትሐዊ ዋጋ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።”
ኢትዮጵያ ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት የዘለለ ራዕይ አንግባ ያለቁ የከበሩ ድንጋዮች አቅራቢ የመሆን የረጅም ግዜ ዕቅድ እንዳላትም ባለሙያው ገልፀዋል፡፡
“እንደ ስልታዊ ዕቅድ የተያዘው እሴት ለተጨመረባቸው የወጪ ንግዶች ማበረታቻ መስጠት ነው፡፡...ለጊዜው ኢትዮጵያ የገበያ ተደራሽነትን በማረጋገጥ እና የሀገር ውስጥ የማቀነባበር አቅምን እያሳደገች፤ ጥሬ እና ያለቁ ኦፓሎችን ለመገበያየት የኢትዮጵያ ምርት ገበያን ትጠቀማለች። የረጅም ጊዜ ራዕዩ ኢትዮጵያን ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወደ ያለቁ የከበሩ ድንጋዮች አምራችነት በማሸጋገር፤ በብሪክስ እና በዓለም አቀፍ ገበያዎች ውስጥ ተወዳዳሪ ሆና እንድትገኝ ማድረግ ነው።”
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X