የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ከጅቡቲ አቻው ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረመ
15:19 24.12.2025 (የተሻሻለ: 15:24 24.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ከጅቡቲ አቻው ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረመ
ሁለቱ አካላት በሲቪል አቪዬሽን ዘርፍ ቴክኒካዊ፣ አስተዳደራዊ፣ ድርጅታዊ እና ተግባራዊ ትብብርን ለማዳበር ስምምነት ላይ ደርሠዋል።
በሌላ በኩል በአቪዬሽን ደህንነት፣ በአቪዬሽን ጥበቃ፣ በአካባቢ ጥበቃ ዘላቂነት፣ በኢኮኖሚ ፖሊሲዎች፣ በሎጅስቲክስ አገልግሎቶች፣ በአየር ትራንስፖርት ጥራት እና በኦዲት ሥራዎች ዙሪያ በጥምረት ለመሥራት መግባባት ላይ እንደደረሱ ከባለሥልጣኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ስምምነቱ የልምድ እንዲሁም የሳይንሳዊ እና ቴክኒካዊ መረጃዎች ልውውጥ ያካትታልም ተብሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X