ሩሲያ ባለ ከፍተኛ ጥራት የጨረቃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ልትገነባ ነው

ሰብስክራይብ

ሩሲያ ባለ ከፍተኛ ጥራት የጨረቃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ልትገነባ ነው

የሩሲያ የጠፈር ኤጀንሲ ሮስኮስሞስ፤ የጨረቃ ተሽከርካሪዎች፣ ሳይንሳዊ የምርምር ጣቢያዎች እና ዓለም አቀፍ የጨረቃ ምርምር ጣቢያ መሠረተ ልማትን ለመሳሰሉ ቁልፍ የሩሲያ የጨረቃ ፕሮግራም ሥራዎች አስተማማኝ እና ዘላቂ ኃይል ለማቅረብ የሚያስችል ትልቅ ስምምነት ተፈራርሟል።

ውሉ እ.ኤ.አ በ2025 እና በ2036 መካከል ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ መርኃ-ግብር ተይዞለታል።

ይህ ግዙፍ ፍኖተ ካርታ የሚከተሉትን ያካትታል፦

የላቁ የጠፈር መንኮራኩሮችን መንደፍ፣

ተከታታይ የመሬት ሙከራ እና ምርምር ማካሄድ፣

የበረራ ላይ ሙከራዎች፣

ጨረቃ ላይ በቀጥታ የተሟላ መሠረተ ልማት መዘርጋት።

"ፕሮጀክቱ ዘላቂ የሆነ ሳይንሳዊ የጨረቃ ጣቢያ ለማቋቋም እና ከአንድ ጊዜ ተልዕኮዎች ወደ የረጅም ጊዜ የጨረቃ ምርምር ፕሮግራም ለመሸጋገር ወሳኝ እርምጃ ነው" ሲል ሮስኮስሞስ ገልጿል።

ሩሲያ እ.ኤ.አ እስከ 2030 ድረስ በሂደት ዓለም አቀፉን የጠፈር ጣቢያ መጠቀም አቁማ ወደ ራሷ ብሔራዊ የምሕዋር ጣቢያ ለመሸጋገር ማቀዷን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ዴኒስ ማንቱሮቭ ባሳለፍነው ሰኔ ወር ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0