ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶችን የሚያግደው መመሪያ ከጥር 23 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ
17:02 23.12.2025 (የተሻሻለ: 17:04 23.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ምርቶችን የሚያግደው መመሪያ ከጥር 23 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ
የፕላስቲክ ምርቶችን ማምረት፣ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባትና ይዞ መገኘት የሚከለክለው አዋጁ ከሐምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ መጽደቁ ይታወሳል፡፡ ባለሥልጣኑ የስድስት ወራት ሽግግር ጊዜ መስጠቱም የሚታወቅ ነው፡፡
የሽግግር ጊዜው ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚያበቃ የገለጹት የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ዴስክ ኃላፊ ዋሲሁን ዓለሙ፤ ከዚህ ዕለት በኋላ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴ ላይ የሚገኙ አካላት ተጠያቂ እንደሚሆኑ አሳስበዋል።
አዋጁ እንደወጣ የፕላስቲክ ስርጭት ቀንሶ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ግን በድጋሚ በገበያው ውስጥ በስፋት እየታየ ነውም ተብሏል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X