ሱዳን ተመድ የሚታዘበው የተኩስ አቁም እቅድ ይፋ አደረገች፤ የፈጥኖ ደራሹ ኃይሉ እንዲያፈገፍግ ጠየቀች
16:38 23.12.2025 (የተሻሻለ: 16:44 23.12.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሱዳን ተመድ የሚታዘበው የተኩስ አቁም እቅድ ይፋ አደረገች፤ የፈጥኖ ደራሹ ኃይሉ እንዲያፈገፍግ ጠየቀች
አማፂያኑ በተለዩ ካምፖች እንዲሠባሠቡና እና በዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ፊት ትጥቅ የመፍታት ሂደት እንዲጀምሩ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ካሚል ኢድሪስ አሳስበዋል።
"በመጀመሪያ በተመድ፣ በአፍሪካ ኅብረት እና በአረብ ሊግ የጋራ ቁጥጥር ስር ሁሉን አቀፍ የተኩስ አቁም ያስፈልጋል። የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች (አርኤስኤፍ) ከተቆጣጠሯቸው አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ለቀው መውጣት አለባቸው" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ይህ ተነሳሽነት በሽግግር ወቅት የሚካሄድ የሱዳን ባለድርሻ አካላት ውይይትንም ያካትታል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
"የሽግግር ግዜው ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በሚሳተፉበት ምርጫ ይጠናቀቃል" ሲሉ ኢድሪስ አክለዋል።
የሱዳን ጦር መጋቢት 16 ካርቱም ሙሉ በሙሉ ከአርኤስኤፍ ቁጥጥር ነፃ መውጣቷን ቢያውጅም አማጺ ቡድኑ በሚያዝያ ወር መጀመሪያ በዳርፉር እና በኮርዶፋን እንቅስቃሴውን አጠናክሮ በመቀጠል ትይዩ አስተዳደር መሥርቷል። ይህ ድርጊት በሕጋዊው የሱዳን መንግሥት እና በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ውግዘት አስከትሏል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X