የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባዔ በመጪው ጥር ወር መጨረሻ ይደረጋል ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባዔ በመጪው ጥር ወር መጨረሻ ይደረጋል ተባለ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባዔ በመጪው ጥር ወር መጨረሻ ይደረጋል ተባለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.12.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባዔ በመጪው ጥር ወር መጨረሻ ይደረጋል ተባለ

ኮሚሽኑ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰጠው የሥራ ጊዜ እስከ የካቲት አጋማሽ 2018 ዓ.ም ድረስ ነው። በዚህም መሠረት ለዋናው ጉባዔ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችና የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ከወዲሁ እየተከናወኑ መሆኑን ኮሚሽነሩ መስፍን አርዓያ ለሚዲያ አስረድተዋል።

ከ4 ሺህ በላይ ተወካዮች በጉባዔው ላይ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ኮሚሽኑ እስካሁን ከትግራይ በስተቀር በሁሉም አካባቢዎች አጀንዳዎችን የማሰባሰብና ተሳታፊዎችን የመለየት ሥራዎችን አከናውኗል።

በትግራይ ክልል የተሳታፊዎች ልየታ፣ የአጀንዳ ማሰባሰብ እና ተወካዮችን የማስመረጥ ሥራዎች ቅደመ ዝግጀት በያዝነው ሳምንት እንደሚጀመር እና የምክክር ሥራው እስከ ታህሳስ 30 ቀን  እንዲጠናቀቅ አቅጣጫ ተቀምጧል ሲሉም ተናግረዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0