- Sputnik አፍሪካ, 1920
Sovereignty Sources
ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

አፍሪካ፡ በባለ ብዙ ወገን ዓለም ውስጥ እያደገ ያለ አህጉር

አፍሪካ፡ በባለ ብዙ ወገን ዓለም ውስጥ እያደገ ያለ አህጉር
ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ሩሲያ ግንኙነት የእኩልነት መርህን መሰረት ያደርገ ነው '' ሉዓላዊ ትብብር የአፍሪካን ሉዓላዊነት እንደሚያመጣ ማየት ትችላላችሁ። ይህ የጌታና አሽከር ወይም የፈረስና ጋላቢ ግንኙነት አይደለም። የጋራ እሴቶች ባላቸው ህዝቦች መካከል ያለ ግንኙነት ነው። እነዚህ የጋራ እሴቶች ሉዓላዊ አፍሪካን ለመፍጠር እንዲሁም ሉዓላዊ የሩሲያ ፌዴሬሽንን ለማበረታታት የምንጠቀምባቸው ናቸው'' ሲሉ የዙምባቡዌ የውጭ ግንኙነትና ዓለምአቀፍ ንግድ ሚኒስትር ፕሮፌሰር አሞን ሙሩዊራ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ሶስት አንኳር ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ አፍሪካ በባለ ብዙ ወገን ዓለም ያላት ሚናን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የዓመቱ ማጠቃለያ ንግግር ጋር በማጣመር በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናቶች ረዳት ፕሮፌሰሩ ሙከረም ሚፍታህ (ዶ/ር) ጋር እንወያያለን። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ ከታህሳስ 19 - 20፣ 2025 በካይሮ፣ ግብፅ የተደረገውን 2ኛው የሩሲያ - አፍሪካ የሚኒስትሮች ጉባዔን የደቡብ ሱዳን የዉጭ ግንኙነትና ዓለምአቀፍ ትብብር ሚኒስትር መንዴይ ሲማያ ኩምባ ፣ እና የዛምቢያ የዉጭ ግንኙነትና ዓለማአቀፍ ትብብር ሚኒስትር ሙላምቦ ሄምቤን አነጋግረናቸዋል። ፀረ - ቅኝ ግዛትና ተያያዥ ጉዳዮችን ከዓለም የፖለቲካና ፍልስፍና ተንታኙ ጋብርዔል አሱኮ ጋር በሶስተኛው ክፍል ቃኝተነዋል።

''የአፍሪካ ሀገራት በምጣኔ ሐብት ዕድገት፣ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች መሻሻል እያሳዩ ነው። ሉዓላዊነት አስፈላጊ ነገር ነው — እንደ ራሲያ እና ቻይና ያሉ ሀገራት ብሪክስም እየጎለበተ መምጣታቱ ባለአንድ ወገኑን ዓለም የመታደስ ግዴታ ውስጥ እያስገባው ነው ''ሲሉ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናቶች ረዳት ፕሮፌሰሩ ሙከረም ሚፍታህ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezer Spotify Podcast AddictPocket CastsAfripodsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0