የኢትዮጵያ ልዑክ ከሶማሊላንድ ጋር የንግግድ ትስስር የማጠናከር ዓላማ ያነገበ ጉብኝት በበርበራ ወደብ አደረገ
13:04 23.12.2025 (የተሻሻለ: 13:14 23.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ልዑክ ከሶማሊላንድ ጋር የንግግድ ትስስር የማጠናከር ዓላማ ያነገበ ጉብኝት በበርበራ ወደብ አደረገ
የክልል እና የፌዴራል መንግሥት ተወካዮችን ያካተተው ልዑክ በበርበራ ነፃ የኢኮኖሚ ዞን የወደብ ተቋማትን፣ የጉምሩክ ሥራዎችን እንዲሁም ቁልፍ የትራንስፖርት እና የሎጂስቲክስ መሠረተ ልማቶችን ጎብኝቷል።
ጉብኝቱ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ግዛት ውስጥ ያለ ዓለም አቀፍ እውቅና ራሷን እያስተዳደረች በምትገኘው ሶማሊላንድ መካከል እያደገ የመጣውን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው ተብሏል፡፡
በተጨማሪም ጉብኝቱ በርበራ፤ ለወጪ እና ገቢ ንግድ አማራጭ ኮሪዶር በማቅረብ እና አጠቅላይ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደትን በመደገፍ፤ ወደብ አልባ ለሆነችው ኢትዮጵያ ወሳኝ የንግድ መግቢያ በር እንደሆነ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X