ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ፍጥነት እና ቅልጥፍናን ያላብሳል - የዘርፉ ምሁር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ፍጥነት እና ቅልጥፍናን ያላብሳል - የዘርፉ ምሁር
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ፍጥነት እና ቅልጥፍናን ያላብሳል - የዘርፉ ምሁር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.12.2025
ሰብስክራይብ

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ፍጥነት እና ቅልጥፍናን ያላብሳል - የዘርፉ ምሁር

መንግሥት በቅርቡ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በይፋ ሥራ መጀመሩን አስታውቋል። በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ለስፑትኒክ አፍሪካ አስተያየታቸውን የሰጡት በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ የኮምፒዩተር ሳይንስ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሺዓለም ገዛኸኝ፤ ከዘርፉ በአግባቡ ለመጠቀም በሀገሪቱ የዲጂታል እውቀት እንዲያድግ መሠራት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

“በዲጂታል ውስጥ ያላለፈ፣ በአግባቡ መጠቀም የማይችል በኢኮኖሚም ይሁን በማንኛውም ነገር ተወዳዳሪ መሆን አይችልም። ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ይህንን አውቆ በዲጂታል ዘርፉ ግንዛቤ መፍጠር፣ ሥልጠና መውሰድ፣ አቅም በመገንባት ሀገሪቱ በዲጂታል ዘርፉ የምታመጣውን እድል መጠቀም ያስፈልጋል ብዬ አስባለሁ” ብለዋል።

የዲጂታል ሉዓላዊነትን በተመለከተ ያነሱት ባለሙያው፤ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ራሳን መቻል እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

“ራስን መቻል ሲባል የመጀመሪያው ነገር፤ የሰው ኃይልን ማሠልጠንና ቴክኖሎጂውን እንዲያውቁት ማድረግ ያስፈልጋል። ስለዚህ ቴክኖሎጂውን ከየት ተነስቶ ምንድን ላይ ነው ያለው? የቴክኖሎጂው ክፍተት ምንድን ነው? ከውጭ የምናስገባቸውን ወሳኝ የሆኑ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎች መቀነስ እና በሀገር ውስጥ መተካት የሚያስፈልግ ይመስለኛል፡፡”

በሌላ በኩል በተለይም በቅኝ ግዛት ስር የነበሩ የአፍሪካ ሀገራት እስካሁን ድረስ የቴሌኮም፣ ፋይናንስ እና ሌሎችም ተቋማት መረጃቸው ከሀገር ውጪ መሆኑ የሚፈጥረውን ጥገኝነት በማንሳት ምክራቸውን ለግሠዋል፡፡

“የራሳችን ኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ አለን... የራሳችን ክላውድ፣ የራሳችን ዳታ ሴንተሮች፣ የራሳችን የአደጋ ማገገሚያ እየገነባን በራሳችን አቅም መፍጠር አለብን። ምክንያቱም በኢኮኖሚ ጥገኛ ከሆንን፤ እነዚህ ሀገራት አጠቃላይ ሁሉን ነገር ያቀርቡልናል፤ ነገር ግን መረጃችን እነሱ ጋር ነው የሚሆነው። ስለዚህ ያ እንዳይሆን...ሙሉ የሀገሪቱ መረጃ እዚሁ በሀገር ውስጥ እየተገነባ፣ ደህንነቱ ደግሞ በደንብ እየተጠበቀ፣ አቅም ግንባታ እየተደረገ፤ ሙሉ በሙሉ በሀገሪቱ ቁጥጥር ስር መሆን አለበት ብዬ አስባለሁ።”

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0