ሶማሊያ ከ50 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የማዘጋጃ ቤት ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅቷን አጠናቀቀች
10:55 23.12.2025 (የተሻሻለ: 11:04 23.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሶማሊያ ከ50 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የማዘጋጃ ቤት ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅቷን አጠናቀቀች
በመጪው ሐሙስ በሞቃዲሾ የሚካሄደውን የማዘጋጃ ቤት ምርጫ ደህንነት ለማረጋገጥ ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ የፖሊስ መኮንኖች ይሠማራሉ።
የሶማሊያ የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትር አብዱላሂ ሼክ ኢስማኢል፤ አስፈላጊው ዝግጅት በሙሉ ሙሉ "ተጠናቋል" ሲሉ ተናግረዋል።
የፖሊስ መኮንኖች የመራጮችን፣ የምርጫ ጣቢያዎችን፣ የምርጫ አስፈጻሚዎችን እና ለአደጋ ተጋላጭ መሠረተ ልማቶችን ደህንነት ለማረጋገጥ በዋና ከተማው እንደሚሠማሩ አብራርተዋል።
ምርጫው በአንድ ሰው አንድ ድምጽ መርህ ላይ ተመሥርቶ በሞቃዲሾ ከ50 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ የሚካሄድ ቀጥተኛ ምርጫ ነው። በምርጫው ከ1 ሺህ 600 በላይ ዕጩዎች ለ390 የአካባቢ መቀመጫዎች ይወዳደራሉ። ወደ 400 ሺህ የሚጠጉ የተመዘገቡ መራጮች ይመርጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የሶማሊያ የምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X