የአካባቢ ጥበቃ ቡድኖች በአፍሪካ ዋንጫ ስፖንሰርሺፕ ምክንያት ለቶታል ኢነርጂስ ‘ቀይ ካርድ’ አሳዩ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአካባቢ ጥበቃ ቡድኖች በአፍሪካ ዋንጫ ስፖንሰርሺፕ ምክንያት ለቶታል ኢነርጂስ ‘ቀይ ካርድ’ አሳዩ
የአካባቢ ጥበቃ ቡድኖች በአፍሪካ ዋንጫ ስፖንሰርሺፕ ምክንያት ለቶታል ኢነርጂስ ‘ቀይ ካርድ’ አሳዩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.12.2025
ሰብስክራይብ

የአካባቢ ጥበቃ ቡድኖች በአፍሪካ ዋንጫ ስፖንሰርሺፕ ምክንያት ለቶታል ኢነርጂስ ‘ቀይ ካርድ’ አሳዩ

​ በርካታ መንግስታዊ ያልሆኑ የአካባቢ ጥበቃ ድርጅቶች ጥምረት፣ በሞሮኮ እየተካሄደ ያለውን የአፍሪካ ዋንጫ ስፖንሰር በማድረጉ በፈረንሳዩ ግዙፍ የነዳጅ ኩባንያ ላይ የተቃውሞ ዘመቻ ጀምረዋል። ቡድኖቹ ኩባንያውን በ"ግሪን ዎሺንግ" (የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪ መስሎ መታየት) እና የሰብአዊ መብት ጥሰት በመፈጸም ከሰውታል።

​ግሪንፒስ አፍሪካ፣ ማጋምባ ኔትወርክ  እና ኪክ ፖሉተርስ አውት የተባሉትን ቡድኖች ያካተተው ይህ ጥምረት፣ ኩባንያው "የአፍሪካ እግር ኳስን ለራሱ መጠቀሚያ ማድረጉን" በመቃወም የፌዝ ቪዲዮ ለቅቀዋል።

​ አህጉሪቱ በከፋ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋ ውስጥ ባለችበት ወቅት፣ አንድ "የኒዮ-ኮሎኒያል አካል የሆነ ግዙፍ የነዳጅ ኩባንያ" በዓለም ተወዳጅ በሆነው የእግር ኳስ ውድድር ስሙን ለማደስ መሞከሩ አሳፋሪ ነው ሲሉ ይከራከራሉ።

​"ግሪን ዋሺንግ" የችግሩ አንድ ገጽታ ብቻ መሆኑን የገለጹት ተሟጓቾች ገልፀዋል።

ቶታል ኢነርጂስ በአፍሪካ በሚያከናውናቸው ፕሮጀክቶች ላይ ያላቸውን ሰፊ ቅሬታ በሚከተሉት ነጥቦች ዘርዝረዋል

​🟠 ከምስራቅ አፍሪካ የነዳጅ መስመር ዝርጋታ ጋር ተያይዞ የሚከሰት የህዝብ መፈናቀል፣

🟠 የመሬት ዝርፊያ እና

🟠 መጠነ-ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች።

​የ2025ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ባለፈው እሁድ በሞሮኮ የተከፈተ ሲሆን፣ ውድድሩ እስከ ጥር 10 ድረስ ይካሄዳል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0