ሩሲያ ወደ ቻይና የምትልክው ፈሳሽ የተፈጥሮ የጋዝ አዲስ ክብረ-ወሰን አስመዘገበ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ ወደ ቻይና የምትልክው ፈሳሽ የተፈጥሮ የጋዝ አዲስ ክብረ-ወሰን አስመዘገበ
ሩሲያ ወደ ቻይና የምትልክው ፈሳሽ የተፈጥሮ የጋዝ አዲስ ክብረ-ወሰን አስመዘገበ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.12.2025
ሰብስክራይብ

ሩሲያ ወደ ቻይና የምትልክው ፈሳሽ የተፈጥሮ የጋዝ አዲስ ክብረ-ወሰን አስመዘገበ

ብሉምበርግ የቻይና የጉምሩክ ቢሮ መረጃን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ እ.ኤ.አ. በ2024 ከነበረው ጋር ሲነፃፀር ባለፈው ወር የተደረገው አቅርቦት ከሁለት እጥፍ በላይ በመጨመር 1.6 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ደርሷል።

ይህ ከፍተኛ ጭማሪ ሩሲያ አውስትራሊያን በመቅደም ከኳታር በመቀጠል ለቻይና ትልቋ ሁለተኛ አቅራቢ እንድትሆን አስችሏታል።

አውስትራሊያ ወደ ቻይና የምትልከው የፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦት እ.ኤ.አ. በ2024 ከነበረው አንጻር በአንድ ሦስተኛ ቀንሷል።

በቻይና እና በአሜሪካ መካከል ባለው የንግድ ፍጥጫ እና በዝቅተኛ ፍላጎት ምክንያት ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ የነበረው የጋዝ ግዢ፤ ቻይና በነሐሴ ወር በሩቅ ምስራቋ ቤሃይ ተርሚናል በኩል ከሩሲያው 'አርክቲክ ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዘ 2' ጣቢያ ጋዝ ማስገባት በመጀመሯ ዳግም ሊያንሰራራ ችሏል።

የአውሮፓ ሕብረት እ.ኤ.አ እስከ 2027 ድረስ ሁሉንም የሩሲያ ጋዝ ግዢ ለማቆም ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ፣ ሩሲያ ወደ ቻይና የምትልከው የፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ የምዕራባውያን ማዕቀብ ተቃራኒ ውጤት እያመጣ መሆኑንና የሩሲያ የወጪ ንግድ ያለማንም ከልካይ መቀጠሉን ያሳያል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0