ሳምሪታን ቀዶ ሕክምና ማዕከል ለመጀመሪያ ጊዜ በማሽን የተቆረጠ እጅን በተሳካ ሁኔታ መቀጠል መቻሉን አስታወቀ
14:36 22.12.2025 (የተሻሻለ: 14:44 22.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሳምሪታን ቀዶ ሕክምና ማዕከል ለመጀመሪያ ጊዜ በማሽን የተቆረጠ እጅን በተሳካ ሁኔታ መቀጠል መቻሉን አስታወቀ
የማእከሉ የአጥንት ቀዶ ሕክምና የከፍተኛ አደጋዎች እና መገጣጠሚያ ቅየራ ሰብ-ስፔሻሊስት ዶ/ር ቢኒያም ተሾመ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የተቆረጠ እጅን ለመቀጠል የተደረጉ የቀዶ ሕክምናዎች አለመኖራቸውን ለአገር ውስጥ የግል ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
አደጋው የደረሰው የሥጋ ማሽን ለማስተካከል ይሞክር በነበረ የ20 ዓመት ወጣት ላይ ነው፡፡
"እጁን ሙሉ በሙሉ ቆርጦትም አልቆመም፣ ደረቱን ቀዶታል፣ ወደ ውስጥ አለመግባቱ ነው እንጂ የደረቱ ጉዳት ከፍተኛ ነበር የሚሆነው።" ሲሉ ሐኪሙ የጉዳቱን ሁኔታ አብራርተዋል፡፡
ተጎጂው በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም መሄዱ፣ ጤና ተቋሙም የሚፈሰውን ደም አስቁሞ የተቆረጠውን እጅ በረዶ ውስጥ ማስቀመጡ ዳግም ለመቀጠል ወሳኝ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።
6 ሠዓት የወሰደው ቀዶ ሕክምናው በስኬት ቢጠናቀቀም ቀጣይ የሕክምና ከትትሎች አስፈላጊ መሆናቸውንም ሐኪሞቹ ጠቁመዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/3
© telegram sputnik_ethiopia

2/3
© telegram sputnik_ethiopia

3/3
© telegram sputnik_ethiopia
1/3
© telegram sputnik_ethiopia
2/3
© telegram sputnik_ethiopia
3/3
© telegram sputnik_ethiopia