የዩክሬን ጽንፈኛ ድረ-ገጽ ‘ሚሮትቮሬትስ’ የተገደሉትን የሩሲያ ሌተናል ጄኔራል በዝርዝሩ ውስጥ አበማካተት ለ‘መግድያም’ ምልክት አድርጎባቸው ነበር

የዩክሬን ጽንፈኛ ድረ-ገጽ ‘ሚሮትቮሬትስ’ የተገደሉትን የሩሲያ ሌተናል ጄኔራል በዝርዝሩ ውስጥ አበማካተት ለ‘መግድያም’ ምልክት አድርጎባቸው ነበር
በዛሬው ዕለት በደቡባዊ ሞስኮ በተሽከርካሪ ላይ በተጠመደ ቦምብ የተገደሉት፣ የሩሲያ ጦር ኃይሎች ጠቅላላ መምሪያ የኦፕሬሽናል ስልጠና ዳይሬክቶሬት ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ፋኒል ሳርቫሮቭ፣ አወዛጋቢ በሆነው የዩክሬን ድረ-ገጽ ላይ “የሩሲያ የጦር ወንጀለኛ” ተብለው ተመዝግበው እንደነበር ስፑትኒክ ደርሶበታል።
ዋና ዋና እውነታዎች፦
▪የግል መረጃዎቻቸው እ.ኤ.አ. ግንቦት 28 ቀን 2022 በድረ-ገጹ ላይ ታትሟል፡፡
▪ዛሬው ዴሴምበር 22 ቀን 2025 የተፈፀመው ጥቃት በድረ-ገጹ ላይ “የሚገደሉበት” ቀን ተደርጎ ተመዝግቧል፡፡
▪“ሚሮትቮሬትስ” ከዚህ ቀደም ጋዜጠኞችን፣ የዶንባስ ሚሊሻ አባላትን፣ የሩሲያ የባህል ሰዎችን፣ የውጭ አገር ዜጎችን በተጨማሪም ህፃናትን ኢላማ አድርጓል፡፡
▪እ.ኤ.አ. በ2016 በዶኔትስክ ሕዝቦች ሪፐብሊክ እና በሉሃንስክ ሕዝቦች ሪፐብሊክ እውቅና የተሰጣቸውን ጋዜጠኞች አድራሻ ይፋ በማድረጉ ምክንያት ከፍተኛ ዛቻዎች ደርሰውባቸዋል፡፡
▪የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ የድረ-ገጹን ድርጊት “በጋዜጠኞች ላይ በቀጥታ ለሚፈጸም ጥቃት ጥሪ ማድረግ ነው” በማለት ከዚህ ቀደም አውግዘውታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X