"የአፍሪካ መሪዎች የሩሲያ ትብብር አኅጉራዊ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ብለው ያምናሉ" - የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
21:02 21.12.2025 (የተሻሻለ: 21:04 21.12.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
"የአፍሪካ መሪዎች የሩሲያ ትብብር አኅጉራዊ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ብለው ያምናሉ" - የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
"የዚህ ጉባኤ አስፈላጊነት የሩሲያ ፌዴሬሽን ለአፍሪካ በጣም ታሪካዊ ወዳጅ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የመጣ ነው። ለአፍሪካ በጣም ስትራቴጂካዊ አጋር ነው" ሲሉ መንዴይ ሴማያ ኩምባ፤ በካይሮ ከተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ የሚኒስትሮች ጉባኤ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ መድረኩ "ተግባራዊ እና ጠቃሚ" ውጤቶችን አስገኝቷል ብለዋል። ሀገራቸው የጉባዔውን ውጤቶች ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።
ለጁባ ትልቅ ውጤት የነበረው በኩምባ እና በሩሲያ አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ መካከል የተደረገው የሁለትዮሽ ስብሰባ ነበር። ሚኒስትሮቹ የሁለቱን ሀገራት ወዳጃዊ ግንኙነት ገምግመው፤ በቅድሚያ የትኩረት መስኮች ትብብር ለማሳደግ ተስማምተዋል፦
🟠 የኢኮኖሚ ትብብር እና ኢንቨስትመንት፣
🟠 የፖለቲካ ልውውጦች እና አቅም ግንባታ፣
🟠 የንግድ እና የቴክኒክ ልውውጦች፣
🟠 በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ እርስ በርስ መደጋገፍ።
ሚኒስትር ኩምባ፤ ለጉባኤው አዘጋጆች የሩሲያ እና ግብፅ መንግሥታት ምሥጋናቸውን አቅርበው፤ ለአፍሪካ የጋራ ተግዳሮቶች የጋራ መፍትሄዎችን ለማምጣት መንገድ ይጠርጋል ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X