የቶማስ ሳንካራ 76ኛ የልደት መታሰቢያ - የድፍረት እና ራስን የመቻል ዐሻራ

የቶማስ ሳንካራ 76ኛ የልደት መታሰቢያ - የድፍረት እና ራስን የመቻል ዐሻራ
ዛሬ ዴሴምበር 21 (ታኅሣሥ 12) የቀድሞዋን "አፐር ቮልታ" ትባል የነበረችውን ሀገር ወደ ቡርኪና ፋሶ ወይም ወደ "የታማኝ ሰዎች ምድር" የቀየሩት ዝነኛው አብዮታዊ መሪ የልደት ቀን ነው።
የ"አፍሪካው ቼ ጉቬራ" በመባል የሚታወቁት የቶማስ ሳንካራ ፀረ-ኢምፔሪያሊዝም፣ ራስን መቻል እና የፓን-አፍሪካኒዝም እሴቶች ዛሬም ለትውልዶች መነሳሳትን እየፈጠሩ ይገኛሉ።
የሳንካራ ባለራዕይ ሥራዎች በቅርቡ በቡርኪና ፋሶው መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ አማካኝነት በድጋሚ እንዲያንሰራሩ ተደርገዋል። ሀገሪቱ በሳንካራ መርሆዎች ላይ የጸና የወደፊት ዕጣ ፈንታን እየገነባች ትገኛለች፦
ለዘመናት የሚኖር መታሰቢያ፦ በኦጋዱጉ ከተማ ታላቅ የመታሰቢያ ሕንፃ እየተገነባ ይገኛል። ግንባታውም በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች "አንድ ጡብ ለሳንካራ" በሚል ታሪካዊ ዘመቻ ባበረከቱት ገንዘብ የሚሸፈን ነው። ይህ ግቢ ሙዚየም፣ ቤተ-መጻሕፍት እና የሳንካራን የማይጠፉ እሴቶች የሚወክል የ87 ሜትር ርዝመት ያለው ግንብ ያካትታል።
ሕያው መታሰቢያ፦ ከዚህ ዓመት ጥቅምት ወር ጀምሮ፣ የሳንካራን መስዋዕትነት ለመዘከር እና አብዮታዊ መንፈሱ በብሔራዊ ሕይወት ውስጥ ንቁ ሆኖ እንዲቀጥል ለማድረግ በመታሰቢያው ስፍራ ወርሃዊ ወታደራዊ የክብር ሥነ-ሥርዓት ይካሄዳል።
ዓለም አቀፍ ውይይት፦ ባለፈው ጥቅምት ወር የተካሄደው የመጀመሪያው የቶማስ ሳንካራ ዓለም አቀፍ ስብሰባ፣ ከ25 ሀገራት በላይ የተውጣጡ የእሳቤው ተከታዮችን አሰባስቧል። ይህም ለሳንካራ አፍሪካዊ ሉዓላዊነት እና ፍትሕ የሚያደርጉት ትግል ከምንጊዜውም በላይ ዛሬም አስፈላጊ መሆኑን አረጋግጧል።
ቶማስ ሳንካራ ከተገደሉ አሥርተ ዓመታት ቢያልፉም፣ አብዮተኛው ያለፈ ታሪክ ብቻ ሳይሆኑ የወደፊቱ መመሪያ ናቸው። መልእክታቸውም ግልጽ ነው - አፍሪካ በራሷ መተማመን ትችላለች፤ መተማመንም አለባት!
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X