የሳሕል ጥምረት ጥምር ኃይል በይፋ ተመረቀ፤ ኮንፌዴሬሽኑ 'የማይቀለበስ እውነታ' ነው ሲሉ የማሊ ፕሬዝዳንት ገለጹ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሳሕል ጥምረት ጥምር ኃይል በይፋ ተመረቀ፤ ኮንፌዴሬሽኑ 'የማይቀለበስ እውነታ' ነው ሲሉ የማሊ ፕሬዝዳንት ገለጹ
የሳሕል ጥምረት ጥምር ኃይል በይፋ ተመረቀ፤ ኮንፌዴሬሽኑ 'የማይቀለበስ እውነታ' ነው ሲሉ የማሊ ፕሬዝዳንት ገለጹ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.12.2025
ሰብስክራይብ

የሳሕል ጥምረት ጥምር ኃይል በይፋ ተመረቀ፤ ኮንፌዴሬሽኑ 'የማይቀለበስ እውነታ' ነው ሲሉ የማሊ ፕሬዝዳንት ገለጹ

​🪖 የማሊ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ባጋራው መግለጫ፣ የሳሕል ሀገራት ጥምረት የተቀናጀ ወታደራዊ ኃይል በብርጋዴር ጄኔራል ዳውዳ ትራኦሬ መሪነት ሥራ ጀምሯል።

አሲሚ ጎይታ በባማኮ በተካሄደው የሰንደቅ ዓላማ ርክክብ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደተናገሩት፣ "አዲሱ የጥምረቱ አዛዥ የታጠቁ የሽብር ቡድኖችን አዳዲስ የአሠራር ዘዴዎች አስቀድሞ ከመረዳት ባለፈ፣ የሳሕል ቀጣናን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ትግል በበላይነት የመምራትና የመቀጠል ኃላፊነት ይኖርበታል" ብለዋል።

​ጎይታ እንደ የሽብር፣ የኢኮኖሚ እና የመረጃ ጥቃቶች ያሉ "በመንግሥታት ከሚደገፉ" ቡድኖች ጥምረቱ ላይ የሚሰነዘሩ ዘርፈ-ብዙ ስጋቶችን ለመከላከል ኮንፌዴሬሽኑ አስፈላጊውን እርምጃ ወስዷል ሲሉ ተናግረዋል።

​ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 2024 ጀምሮ የኒጀር፣ የማሊ እና የቡርኪና ፋሶ የጦር ኃይሎች በርካታ የጋራ ዘመቻዎችን ማድረጋቸውንና ይህም "በርካታ የሽብር ቡድን መሪዎችን ለመደምሰስ" ማስቻሉን የማሊው መሪ አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።

​ለዚህ ስኬት መገኘት ደግሞ "ጥሩ ዕቅድ፣ ወቅታዊ የመረጃ ልውውጥ እና ከሁሉም በላይ ጥረቶችን ማቀናጀት" ትልቅ ድርሻ እንዳበረከተ ጠቅሰዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የሳሕል ጥምረት ጥምር ኃይል በይፋ ተመረቀ፤ ኮንፌዴሬሽኑ 'የማይቀለበስ እውነታ' ነው ሲሉ የማሊ ፕሬዝዳንት ገለጹ - Sputnik አፍሪካ
1/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የሳሕል ጥምረት ጥምር ኃይል በይፋ ተመረቀ፤ ኮንፌዴሬሽኑ 'የማይቀለበስ እውነታ' ነው ሲሉ የማሊ ፕሬዝዳንት ገለጹ - Sputnik አፍሪካ
2/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የሳሕል ጥምረት ጥምር ኃይል በይፋ ተመረቀ፤ ኮንፌዴሬሽኑ 'የማይቀለበስ እውነታ' ነው ሲሉ የማሊ ፕሬዝዳንት ገለጹ - Sputnik አፍሪካ
3/3
1/3
2/3
3/3
አዳዲስ ዜናዎች
0