የሩሲያ-አፍሪካ የማዳበሪያ ትብብር ለምግብ ዋስትና እና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ምሰሶ ነው - የዚምባብዌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

የሩሲያ-አፍሪካ የማዳበሪያ ትብብር ለምግብ ዋስትና እና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ምሰሶ ነው - የዚምባብዌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

በሩሲያ ቴክኖሎጂ እና በአፍሪካ ጥሬ ዕቃዎች በመታገዝ በሀገር ውስጥ ማዳበሪያ ማምረት መቻል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው ሲሉ አሞን ሙርዊራ በካይሮ ከተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ የሚኒስትሮች ጉባዔ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

“ማዳበሪያ ለግብርና አብዮት አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም እኔና አንተ የባዮሎጂ ውጤቶች ነን።...እኛ ከምንም ነገር በፊት ተመጋቢዎች ነን።”

ተነሳሽነቱን “የትብብር 2.0” ቁልፍ አካል ነው በማለት፤ ከፖለቲካዊ አብሮነት በጋራ ወደ ማምርት እንደሚያሻግር ገልፀዋል። “በምርት ሂደት ስትተባበር ማኅበራዊ ግንኙነትንም ማጠናከር ትችላለህ።”

ይህ ትብብር የአፍሪካን የምግብ ነፃነት ከማጠናከር ባለፈ፤ የሩሲያን የአቅርቦት አድማስ እንደሚያሰፋም ከፍተኛ ዲፕሎማቱ አክለዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0