ፕሬዝዳንት ፑቲን በዩሬዥያ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ ነው
16:49 21.12.2025 (የተሻሻለ: 16:54 21.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ፕሬዝዳንት ፑቲን በዩሬዥያ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ ነው
የዩሬዥያ ኢኮኖሚ ሕብረት ከፍተኛ ምክር ቤት የመሪዎች ጉባኤ በዛሬው ዕለት በሴንት ፒተርስበርግ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
ጉባኤውን አስመልክቶ የተሰሙ ዋና ዋና ዝርዝሮች፦
▪ የዩሬዥያ ኢኮኖሚ ሕብረት በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት ሕጋዊ ሰውነት ያለው፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደትን ለመፍጠር የተቋቋመ ዓለም አቀፍ ድርጅት ነው፡፡
▪ የሕብረቱ ሙሉ አባል አገራት፦ ሩሲያ፣ ቤላሩስ፣ ካዛኪስታን፣ አርሜኒያ እና ኪርጊስታን ናቸው፡፤
▪ የሕብረቱ መሪዎች አንገብጋቢ ጉዳዮችን የሚወያዩ ሲሆን፣ በጋራ ገበያ ውስጥ ለሚኖረው ቀጣይ ውህደት መመሪያዎችን ያወጣሉ፤ እንዲሁም አስፈላጊ ሰነዶችንና ውሳኔዎችን ያፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
▪ በሕብረቱ እና በኢንዶኔዥያ መካከል ነፃ የንግድ ስምምነት ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል፤
▪ ቭላድሚር ፑቲን በሴንት ፒተርስበርግ ከኪርጊስታን እና ከቤላሩስ ፕሬዝዳንቶች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚያደርጉ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X