የሩሲያ እና አፍሪካ ትስስር በጫና ሳይሆን በጋራ እሴቶች ላይ የተመሠረተ ነው - የዚምባብዌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

የሩሲያ እና አፍሪካ ትስስር በጫና ሳይሆን በጋራ እሴቶች ላይ የተመሠረተ ነው - የዚምባብዌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

“የጌታ-ጋላቢ ወይም የፈረስ እና የጋላቢ ግንኙነት አይደለም” ሲሉ አሞንግ ሙርዊራ ከሩሲያ-አፍሪካ የሚኒስትሮች ጉባዔ ጎን ለጎን ተናግረዋል። ግንኙነቱ የሁለቱን ወገኖች ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ነፃነት እንደሚያሳድግ አፅንዖት ሰጥተዋል።

ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ “ሉዓላዊ ምርጫዎች ወደ ሉዓላዊ ውጤቶች ያመራሉ” ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ዚምባብዌ የበላይነትን እና የዜሮ ድምር ጨዋታዎችን በመቃወም፤ ለባለብዙ ዋልታ ዓለም፣ ለተባበሩት መንግሥታት ቻርተር መርሆዎች እና ሁሉንም ተጠቃሚ ለሚያደርግ ትብብር ቁርጠኛ እንደሆነች አስረግጠዋል።

በቀጣይ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት አባል መሆን ከመቻሏ አንፃር፤ ዚምባብዌ ዓለም አቀፍ ስርዓትን እንደገና በመቅረፅ ረገድ ቁልፍ አጋር ከሆነችው ሩሲያ ጋር ለቅኝ አገዛዝ መወገድ፣ ለውይይት እና ለክብር ትሟገታለች ሲሉ ተናግረዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0