በጆሃንስበርግ አቅራቢያ የተፈጸመ የጅምላ ተኩስን አስመልክቶ እስካሁን የታወቁ መረጃዎች
13:10 21.12.2025 (የተሻሻለ: 13:14 21.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በጆሃንስበርግ አቅራቢያ የተፈጸመ የጅምላ ተኩስን አስመልክቶ እስካሁን የታወቁ መረጃዎች
በደቡብ አፍሪካ ፖሊስ መግለጫ መሠረት፣ በጆሃንስበርግ አቅራቢያ በተፈፀመ የጅምላ ተኩስ በትንሹ ዘጠኝ ሰዎች ሲገደሉ አሥር ሰዎች መቁሰላቸውን ታውቋል።
በመግለጫው የተነሱ ዋና ዋና ዝርዝሮች፦
▪ ጥቃቱ የተፈጸመው ዛሬ ማለዳ ከጆሃንስበርግ በስተደቡብ ምዕራብ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘ ቤከርስዳል የገጠር ከተማ ውስጥ ነው፡፡
▪ በነጭ ሚኒባስ እና በሲልቨር ሴዳን የቤት መኪና የመጡ ወደ 12 የሚጠጉ የታጠቁ ተጠርጣሪዎች ፈቃድ ባለው የመጠጥ ቤት ውስጥ በነበሩ ደንበኞች ላይ ተኩስ ከፍተዋል፡፡
▪ ጥቃት አድራሾቹ ከአካባቢው በማምለጥ ላይ ሳሉ በጎዳና ላይ ባሉ ሰዎች ላይ የዘፈቀደ ተኩስ ከፍተዋል፡፡
▪ ከሟቾቹ መካከል ከሕንጻው ውጭ ሥራ ይጠባበቅ የነበረ የራይድ አሽከርካሪ ይገኝበታል፡፡
▪ የተወሰኑት ሰዎች በመንገድ ላይ በማይታወቁ ታጣቂዎች ተተኩሶባቸዋል፡፡
▪ የጥቃቱ መንስኤ እስካሁን እንዳልታወቀ ፖሊስ ለፈረንሳይ ሚዲያ ገልጿል፡፡
▪ የጋውቴንግ የከባድ እና የከፍተኛ ወንጀሎች ምርመራ ክፍል ከወንጀል መከታተያ ቡድን ጋር በመሆን መጠነ ሰፊ የአሰሳ ዘመቻ ጀምረዋል፡፡
▪ የቆሰሉ ሰዎች በሙሉ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
/