ማሊ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት አዲስ ፈጥኖ ደራሽ ሻለቃ ጦር አደራጀች
12:21 21.12.2025 (የተሻሻለ: 12:54 21.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ማሊ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት አዲስ ፈጥኖ ደራሽ ሻለቃ ጦር አደራጀች
ልዩ ጦሩ፤ የጦር ኃይሉን ምላሽ የመስጠት አቅም ለማሳደግ፣ ሲቪሎችን ለመጠበቅ እና የሀገሪቱን የግዛት አንድነት የማስከበር ኃላፊነት ተጥሎበታል። የሻለቃው የሰው ኃይል መጠን በይፋ አልተገለፀም። እንደ ሞተር ብስክሌት ያሉ ለደጋማና አስቸጋሪ ሥፍራዎች ተስማሚ የሆኑ ተንቀሳቃሽ መሣሪያዎችን እንደታጠቀ ተገልጿል።
የመከላከያ ሚኒስትሩ ሳዲዮ ካማራ አዲሱ አደረጃጀት በየጊዜው ለሚለዋወጡ ስጋቶች የተሰጠ ቁልፍ ምላሽ ነው ብለዋል። የጦር ኃይሉ ጠቅላይ አዛዥ ኦማር ዲያራ በበኩላቸው፤ በዋና ዋና መንገዶች በወታደራዊ ተሽከርካሪዎችና በሲቪሎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች መበራከታቸው ሻለቃው እንዲቋቋም ምክንያት መሆኑን ጠቅሰዋል።
እ.ኤ.አ ከ2012 ጀምሮ በማሊ በጅሃዲስት አማፂያን እና በጎሳ ግጭቶች ሳቢያ በተባባሰው የደህንነት ቀውስ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለህልፈት የተዳረጉ ሲሆን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩትን ደግሞ ከመኖሪያ ቀዬአቸው አፈናቅሏል።
አዲሱ ክፍለ ጦር ማሊ የሳኅል ቀጣናን ደህንነት ለማጠናከር እያደረገችው ያለው ጥረት ማሳያ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

