🪖 ከተጣሉበት በማንሳት በራስ አቅም ተሻሽለው ወደ ኃይል የገቡት ትጥቆች የተቋሙን የውጊያ አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራሉ –ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
11:32 21.12.2025 (የተሻሻለ: 11:34 21.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
🪖 ከተጣሉበት በማንሳት በራስ አቅም ተሻሽለው ወደ ኃይል የገቡት ትጥቆች የተቋሙን የውጊያ አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራሉ –ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
የመከላከያ ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ሙሉ ዕድሳትና ሙከራ ያደረገላቸውን በርካታ የሜካናይዝድ ትጥቆችን ወደ ኃይል ማስገባቱን አስታውቋል፡፡
“ዋና መምሪያው ሀገርን በቢሊየን ከሚቆጠር ወጪ ከማዳኑ ባለፈ በራስ አቅምና ፈጠራን በማሻሻል ተአምራዊ የሚባል ሥራ መሥራት እንደምንችልም ያሳየ ነው” ሲሉ በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገልጸዋል።
የመከላከያ የሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ጥገናና ሙከራ ያደረገባቸውና ውጤታማነታቸው የተረጋገጡት ትጥቆችን ለመከላከያ የሜካናይዝድ ዕዝ አስረክቧል።
ከኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር የተገኙ ምስሎች
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X






