የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎትን ለመግዛት በርካታ ሀገራት ጥያቄ ማቅረባቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩገሩ
10:06 21.12.2025 (የተሻሻለ: 10:14 21.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎትን ለመግዛት በርካታ ሀገራት ጥያቄ ማቅረባቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩገሩ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገልግሎቱን ለተለያዩ ሀገራት በክፍያ ለማቅረብ ድርድሮች በመደረግ ላይ መሆናቸውን ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ይፋ ባደረጉበት መድረክ ላይ አስታውቀዋል።
🪪 ዛምቢያን ጨምሮ በፍርድ ቤቶች፣ በኢትዮ ቴሌኮም እና በሞሰብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እየተሰጡ ያሉ ግልጋሎቶችን የጎበኙ በርካታ ሀገራት የግዢ ጥያቄ ማቅረባቸውንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት።
ብዙዎቹ የአፍሪካ ሀገራት ከሌሎች የውጭ ሀገራት የሚገዟቸው አገልግሎቶች እየተዘጉባቸው መሆኑን ተከትሎ “የአፍሪካን እንጠቀም የሚል ሐሳብ እየተፈጠረ” መምጣቱንም ገልጸዋል።
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት እስካሁን ከ30 ሚሊዮን በላይ ህዝብን መመዝገቡና እስከ ሰኔ ወር ድረስ 90 ሚሊዮን ለማድረስ እየተሠራ መሆኑን በመድረኩ ላይ ተገልጿል ሲል የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X