ሩሲያ የአፍሪካን ተሰሚነት ከፍ የምታደርግ ጂኦ-ፖለቲካዊ ኃይል ናት – የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ የአፍሪካን ተሰሚነት ከፍ የምታደርግ ጂኦ-ፖለቲካዊ ኃይል ናት – የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር
ሩሲያ የአፍሪካን ተሰሚነት ከፍ የምታደርግ ጂኦ-ፖለቲካዊ ኃይል ናት – የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.12.2025
ሰብስክራይብ

ሩሲያ የአፍሪካን ተሰሚነት ከፍ የምታደርግ ጂኦ-ፖለቲካዊ ኃይል ናት – የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር

አፍሪካ ዳግም የገባችበትን የእጀ አዙር ቅኝ አገዛዝ ለመቀልበስ ከሩሲያ ጋር የሚደረገው ትብብር ወሳኝ መሆኑን በወሎ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህሩ ጀማል ሰይድ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዚህ ረገድ ሩሲያ የአፍሪካን ሉዓላዊነት የምታከብርና በቴክኖሎጂ የምትደግፍ "ጂኦ-ፖለቲካዊ አጋር" መሆኗን በግብፅ የሚካሄደው የሩሲያ አፍሪካ የሚኒስትሮች ጉባኤ እና ባለፉት ዓመታት የተካሄዱት የመሪዎች ጉባኤዎች ማሳያ መሆናቸውን ገልጸዋል።

“ይህ የካይሮ የሩሲያ-አፍሪካ የሚኒስትሮች ጉባኤ፣ ቀደም ሲል በሶቺ እና በሴንት ፒተርስበርግ የተደረጉ ስምምነቶችን ወደ ተግባር በመቀየር አኅጉሪቱን ከተጽዕኖ ነፃ ለማውጣት ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል” ብለዋል፡፡

አፍሪካ የውጭ እርዳታ ጠባቂ ከመሆን ወጥታ "የምታመርተውን መመገብ፣ የምትመገበውን ደግሞ በሀገር ውስጥ ማምረት" እንዳለባት የገለፁት መምህሩ፤ ሩሲያም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከጥገኝነት ይልቅ ራስ መቻልን የምትደግፍ ሀገር መሆኗን አስረድተዋል፡፡

"ሩሲያ የአፍሪካን ሀብት ለመቀራመት ወይም ሉዓላዊነቷን ለመጣስ የማትፈልግ፣ የአፍሪካን ተሰሚነት ከፍ የምታደርግ ጂኦ-ፖለቲካዊ ኃይል ናት" ሲሉም የፖለቲካ ሳይንስ መምህሩ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0