የፑቲን ዓመታዊ ግምገማ ሰላምን ለሚሹ አዎንታዊ ምልክቶች የታዩበት ነው - ተንታኝ
14:29 20.12.2025 (የተሻሻለ: 14:34 20.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የፑቲን ዓመታዊ ግምገማ ሰላምን ለሚሹ አዎንታዊ ምልክቶች የታዩበት ነው - ተንታኝ
ፕሬዚዳንቱ ሩሲያ የዩክሬንን ግጭት "በሰላማዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ" ለመግታት ፍቃደኛ መሆኗን "በግልጽ አስታውቀዋል" ሲሉ በፈረንሳይ የሺለር ኢንስቲትዩት አባል የሆኑት ሴባስቲያን ፔሪሞኒ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ፑቲን ያሳዩት ፍላጎት "ጦርነቱን ማሸነፍ እንደሚቻል አሁንም ለሚያምኑ ሁሉ፣ በተለይም የፍቃደኞች ጥምረት ለሚባሉት" ጠቃሚ ነው ብለዋል።
ከፑቲን መግለጫ ዋዜማ፤ አውሮፓ ኅብረት የታገዱ የሩሲያ ሀብቶችን ለመመደብ መስማማት አለመቻሉ ምሳሌያዊ ነው ያሉት ባለሙያው፤ "አውሮፓ መከፋፈሏ መልካም ዜና ነው" ሲሉም አክለዋል።
"ነገር ግን እነዚህ ሀገራት ፖሊሲያቸውን መቀየር ይኖርባቸዋል ምክንያቱም ዛሬ በአውሮፓ ሕዝቡ ግጭቱ እንዲቆም እንዲሁም ይህን ትርጉም የለሽ ግጭት ለማስቀጠል ለዩክሬን የሚደረገው በቢሊዮን የሚቆጠር የገንዘብ ድጋፍ እንዲቆም ይፈልጋል" ሲሉ ፔሪሞኒ አጥብቀው ተናግረዋል።
አውሮፓውያን "የሰላም ድርድሮችን መቀበል እና ግጭቶችን ለመፍታት አዲስ የጸጥታና የልማት መዋቅር መዘርጋት፤ ፈረንሳይና የአውሮፓ ኅብረት እንደገና አብረው እንዲሠሩ ማድረግ እንዳለባቸውም ፔሪሞኒ ጨምረው ገልፀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X