የሩሲያ-አፍሪካ አጋርነት ፎረም አፍሪካን ጥሬ ዕቃ አቅራቢ ብቻ ሳይሆን ንቁ አጋር መሆኗን ያሳያል - የናሚቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
10:02 20.12.2025 (የተሻሻለ: 10:04 20.12.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ-አፍሪካ አጋርነት ፎረም አፍሪካን ጥሬ ዕቃ አቅራቢ ብቻ ሳይሆን ንቁ አጋር መሆኗን ያሳያል - የናሚቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
በሁለተኛው የሩሲያ-አፍሪካ አጋርነት ፎረም የሚኒስትሮች ጉባኤ ጎን ለጎን የአፍሪካ ሚኒስትሮች ከፍተኛ ተሳትፎ፣ ከሩሲያ ጋር ላለው ግንኙነት ያላቸውን አድናቆት እና የወደፊት ትብብር ላይ ያላቸውን እምነት የሚያሳይ መሆኑን ሴልማ አሺፓላ-ሙሳቪ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። አክለውም እየተለወጠ ባለው የዓለም ሥርዓት ውስጥ ስላለው ተስፋ ያላቸውን ብሩህ አመለካከት ገልጸዋል።
ናሚቢያ ከሶቪዬት ዘመን ጀምሮ ከሩሲያ ጋር የነበራትን አጋርነት ያስታወሱት አሺፓላ-ሙሳቪ፤ በሞስኮና በመላው ሶቪዬት ሕብረት ለወጣት ናሚቢያውያን የተሰጡ የትምህርት ዕድሎችን ጨምሮ ሀገሪቱ በቅኝ ግዛት ወቅት ሰፊ ድጋፍ ታገኝ እንደነበር አስታውሰዋል።
የ35ኛ ዓመት የነፃነት እና የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በዓልን ምክንያት በማድረግ፣ ቁልፍ የትብብር ዘርፎችን አጉልተው አሳይተዋል፦
🟠 ደህንነት
🟠 መከላከያ
🟠 ግብርና
🟠 ማዕድን
🟠 ትምህርት
🟠 ጤና
ናሚቢያ በንግድ እና በክህሎት ሽግግር ላይ ትኩረት እያደረገች መሆኑንና ወጣት ናሚቢያውያን በሩሲያ ኩባንያዎች ውስጥ የሥራ ልምድ እያገኙ መሆናቸውን ሚኒስትሯ አክለው ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X