‘የፑቲን መግለጫ የሩሲያን ወታደራዊ ድልና የኢኮኖሚ ጥንካሬ ያረጋገጠ ነው’ - ባለሙያ
20:38 19.12.2025 (የተሻሻለ: 20:44 19.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
‘የፑቲን መግለጫ የሩሲያን ወታደራዊ ድልና የኢኮኖሚ ጥንካሬ ያረጋገጠ ነው’ - ባለሙያ
መድረኩ ሩሲያ ብሔራዊ ጥቅሟን በጽኑ መሠረት ላይ እንደጣለችና ከዩክሬን ግጭት ጎን ለጎን የሀገሪቱን የኢኮኖሚና ወታደራዊ ጥንካሬ ለዓለም ያሳየችበት ነው ሲሉ በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ መምህርና ተመራማሪ አበራ ሄቢሶ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ፑቲን በመግለጫቸው፤ ሩሲያ ባለፉት ሦስት ዓመታት ከአውሮፓውያን ዕድገት በላይ የ9.7 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት አስመዝግባለች ማለታቸውን ያደነቁት ባለሙያው፤ ሀገሪቱ ማዕቀቦችን ተቋቁማ በሀገር ውስጥ ምርትና በአማራጭ የገበያ ትስስር ራሷን መከላከል መቻሏን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
"ሩሲያ ሉዓላዊነቷን እና ክብሯን ላለማስነካት የምትፈልግ ሀገር በመሆኗ እጅግ በጣም ብዙ መስዋዕትነት ከፍላለች። ያለ አንዳች የውጭ ድጋፍ ጦርነቱን በድል እየተወጣች እንደሆነ ይታየኛል" ሲሉ ተመራማሪው ገልጸዋል።
ፑቲን፣ ኪዬቭ ሰላማዊ መፍትሄ አትሻም ማለታቸውን አስመልክቶ ሀሳባቸውን ያጋሩት ባለሙያው፣ ዩክሬን የሰላም ድርድርን የምትገፋው በምዕራባውያን አለሁልሽ ባይነት ነው ብለዋል፡፡
የኪዬቩ አገዛዝ ራሱን ጠንካራ አድርጎ የሚያቀርበው አጋሮቹን ለማስደሰት ነው ሲሉም ፑቲን በተደጋጋሚ የሚሰጡትን ሀሳብ አጠናክረዋል፡፡
"የዩክሬን አቋም አልተለወጠም የሚሉ ወሬዎች የሀገሪቱን መዳከም ለመደበቅ እንጂ፤ ነባራዊ ሁኔታው ዩክሬን ቀድሞ የነበራት ጥንካሬ ላይ ናት ለማለት የማይቻልበት ነው" ሲሉ አብራርተዋል።
ሩሲያ ከግጭቱ በፊትም ሆነ አሁን ብሔራዊ ጥቅሟን አሳልፋ እንደማትሰጥ ፕሬዚዳንት ፑቲን በድጋሚ ማረጋገጣቸውን ባለሙያው አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X