አውሮፓውያን ግጭቱን በማስቀጠል የዩክሬናውያን ደም እንዲፈስ ነው ፍላጎታቸው - ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ምሁር
19:03 19.12.2025 (የተሻሻለ: 22:04 19.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አውሮፓውያን ግጭቱን በማስቀጠል የዩክሬናውያን ደም እንዲፈስ ነው ፍላጎታቸው - ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ምሁር
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዛሬ ባካሄዱት የዓመቱ ማጠቃለያ ጥያቄ እና መልስ ዝግጅት፤ "የዩክሬን ግጭት መንስኤ ሊፈታ ይገባል" በሚል ከሰጡት አስተያየት እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ፤ ከፍተኛ የፖሊሲ አማካሪ እና የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ አስተያየት ሰጥተዋል።
እንደ ባለሙያው ማብራሪያ፤ ግጭቱ አሁንም እየተካሄደ ያለበት ምክንያት አውሮፓውያን የሚንስክ ስምምነቶችን ለማክበር አሻፈረኝ በማለታቸው እንደሆነ ተናግረዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ልዩ ወታደራዊ ዘመቻዋን የጀመረችው ምዕራቡ ዓለም እና ኔቶ ሞስኮን ለማተራመስ የፖለቲካ ውሳኔ በመውሰዳቸው እንደሆነም አብራርተዋል።
"የአውሮፓ ኅብረት እና ኔቶ...በእርግጥ ሩሲያን ለማተራመስ የፖለቲካ ተነሳሽነት ወስደዋል። ለዚህም ነው ሩሲያ በመጨረሻ ከዩክሬን ጋር ግጭት ውስጥ የገባችው።...አውሮፓውያን እግራቸው ላይ እየተኮሱ ነው። ግጭቱ በመጨረሻም ሲጠናቀቅ የአውሮፓ ኢኮኖሚ፣ የአውሮፓ ሞራል ሙሉ በሙሉ ይዳከማል። በእርግጥ ለዚህ ዋጋ የሚከፍሉት ዩክሬናውያን ናቸው።"
በተጨማሪም ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ፤ በዩክሬን ሰሞኑን ስለተሰማው የሙስና ቅሌት አንስተው የአውሮፓ መሪዎችን ወቅሰዋል።
"የዩክሬን ሕዝብ እንዲፈናቀል እና ስደተኛ እንዲሆን ይፈልጋሉ። የመጨረሻውን ዋጋ የዩክሬን ሕዝብ ነው የሚከፍለው። በዩክሬን የዘለንስኪ ዋና አማካሪ በሀገሪቱ ተቋማት የሙስና ክስ እንደተመሰረተባቸው ሰምተናል። ከዩክሬንም ሸሽተዋል። ስለዚህ እየታየ ያለው አውሮፓውያን ጨዋታ እየተጫወቱ እንደሆነ ነው።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X