ኢትዮጵያና ኬንያ የድንበር ንግድ ስምምነት ተፈራረሙ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያና ኬንያ የድንበር ንግድ ስምምነት ተፈራረሙ
ኢትዮጵያና ኬንያ የድንበር ንግድ ስምምነት ተፈራረሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.12.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያና ኬንያ የድንበር ንግድ ስምምነት ተፈራረሙ

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እና የኬንያ የኢንቨስትመንት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ካቢኔ ሲክሬተሪ ሊ ኪንያንጂዩን በዛሬው ዕለት ስምምነቱን ተፈራርመዋል።

ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)፣ የንግድ እንቅፋቶችን በመቀነስ አነስተኛ መጠን ያለው ድንበር ተሻጋሪ ንግድን የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸዋል።

“... በአሁኑ ጊዜ አብዛኛዎቹን መደበኛ ያልሆኑ ድንበር ተሻጋሪ ነጋዴዎች በተለይም ለሴቶች እና ወጣቶች ግልጽና ሊገመት የሚችል ማዕቀፍ የሚፈጥር ነው፡፡” ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

የጉምሩክ አሠራሮችን ቀላል በማድረግ እና ሰነዶችን በማስማማት ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ሕጋዊ እና ዘላቂ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲፈጠር ያደርጋልም ተብሏል።

ስምምነቱ እ.ኤ.አ ሚያዚያ 17 ቀን 2025 በኬንያ ሞምባሳ የተደረሰበት ስምምነት አካል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በማኅበራዊ የትስስር ገጹ ላይ አስታውቋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0