የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት "አግሪለርን" የተሰኘ የዲጂታል ትምህርት በይፋ አስጀመረ
18:21 19.12.2025 (የተሻሻለ: 18:24 19.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት "አግሪለርን" የተሰኘ የዲጂታል ትምህርት በይፋ አስጀመረ
ይህ አገልግሎት ግብርናን በዲጂታል መንገድ ለማስተማር እና ዘርፉን ሳቢ፣ ተደራሽ እና ለወጣት ኢትዮጵያውያን ተፈላጊ ለማድረግ የተነደፈ መሆኑን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል፡፡
ይህ የዲጅታል የመማሪያ መድረክ ወጣቶች በየትኛዉም ቦታ ሆነዉ በተንቀሳቃሽ ስልካቸዉ ትምህርቱን እንዲከታተሉ እና እውቅና አግኝተዉ ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ ያስችላል ተብሏል፡፡
"አግሪለርን" (AgriLearn) ከመማሪያ መድረክነት ባለፈ ለግብርና ትራንስፎርሜሽን አጋዥ እንደሚሆን የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡
የዲጂታል አገልግሎቱ ከዓለም አቀፍ ተቋም ጋር በመተባበር ወደ ሥራ እንዲገባ መደረጉ ተመላክቷል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X