ፑቲን ከአራት ሠዓታት በላይ በፈጀው የዓመቱ ማጠቃለያ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ያነሷቸው ቁልፍ ነጥቦች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱፑቲን ከአራት ሠዓታት በላይ በፈጀው የዓመቱ ማጠቃለያ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ያነሷቸው ቁልፍ ነጥቦች
ፑቲን ከአራት ሠዓታት በላይ በፈጀው የዓመቱ ማጠቃለያ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ያነሷቸው ቁልፍ ነጥቦች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.12.2025
ሰብስክራይብ

ፑቲን ከአራት ሠዓታት በላይ በፈጀው የዓመቱ ማጠቃለያ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ያነሷቸው ቁልፍ ነጥቦች

ስለ ዩክሬን ግጭት

🟠 ሩሲያ ዩክሬን በግዛት ጉዳይ ላይ ለመወያየት ያላትን ፈቃደኝንት እስካሁን አላየችም። ሞስኮ በበኩሏ ይህንን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለማስቆም ዝግጁ እና ፈቃደኛ ነች።

🟠 እ.ኤ.አ. በ2022 ሩሲያ ዩክሬንን እውቅና የሌላቸውን ሪፐብሊኮች እውቅና ለመስጠት እንደምትገደድ አስጠንቅቃ የነበረ ሲሆን ህዝቡ በሰላም እንዲኖር እንዲፈቀድላት ጠይቃለች።

🟠 ትራምፕ በዩክሬን ያለውን ግጭት ለማስቆም ጠንካራና ከልብ የመነጨ ጥረት እያደረጉ ነው።

🟠 ሞስኮ በአንኮሬጅ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ስለዩክሬን ያቀረቡትን ሐሳብ በተግባር አጽድቃለች።

🟠 ኳሱ ሙሉ በሙሉ በኪዬቭ አገዛዝ መሪ እና በአውሮፓ ደጋፊዎቹ እግር ስር ነው።

🟠 ሩሲያ የዩክሬን ግጭት ለማስቆም የሚቀርቡ የሰላማዊ እልባት ዕቅዶችን ውድቅ ታደርጋለች የሚሉ መግለጫዎች ትክክል ያልሆኑ እና መሠረተ ቢስ ናቸው።

🟠 ሞስኮ በሩሲያ የሚኖሩ ዩክሬናውያን በሩሲያ ግዛት ውስጥ ድምጽ መስጠት እንዲችሉ ትጠይቃለች።

🟠 ሩሲያ በምርጫ ወቅት በዩክሬን ግዛት ላይ ከማንኛውም ጥቃቶች ለመታቀብ ዝግጁ ነች።

ስለ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ

🟠 በኩርስክ ግዛት ውስጥ ጠላት ከተባረረ በኋላ በግንባሩ ላይ ያለው ስትራቴጂያዊ ተነሳሽነት ከሩሲያ ወታደሮች ጋር ነው። ጠላት ከየአቅጣጫው እያፈገፈገ ነው።

🟠 ሴቨርስክን በመያዝ የሩሲያ የጦር ኃይሎች ወደ ስላቭያንስክ መሄድ ይችላሉ።

🟠 የኩፕያንስክ ከተማ በሩሲያ የጦር ኃይሎች ቁጥጥር ስር ነው።

ስለ ሩሲያ ጦር

🟠 የሩሲያ ጦር በዓለም ላይ እጅግ ዝግጁ ሠራዊት ሆኗል።

🟠 700 ሺህ የሩሲያ ወታደሮች በዩክሬን ግንባር እየተዋጉ ነው።

🟠 በ2025 ከ400 ሺ በላይ ዜጎች ወታደራዊ ኃይሉን ለመቀላቀል ከሩሲያ የጦር ኃይሎች ጋር ውል ተፈራርመዋል።

🟠 ወደ ሩሲያ የጦር ኃይሎች የሚገቡ የበጎ ፈቃደኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።

🟠 ሩሲያ በድሮን ዘርፍ መሪ ሆናለች።

ከምዕራቡ ዓለም ጋር ባሉ ግንኙነቶች

🟠 ዋናዋ የኔቶ አባል ሀገር የሆነችው አሜሪካ ሩሲያን ተቀናቃኝ ወይም ጠላት አድርጋ አትመለከትም።

🟠ምዕራባውያን ሩሲያን የሚያከብሩ ከሆነ አዲስ ልዩ ወታደራዊ ዘመቻዎች አይኖሩም። ሩሲያ ከአውሮፓ ጋር ለመዋጋት ምንም ዓላማ የላትም።

🟠 ከምዕራቡ ዓለም ጋር እየተዋጋች ያለችው ሩሲያ ሳትሆን ምዕራባውያን በዩክሬን ብሔርተኞች አማካኝነት ሩሲያን እየተዋጉ ነው። ምዕራባውያን በዩክሬን ያለውን ግጭት በራሳቸው እጅ ፈጥረው ሁኔታውን እያባባሱት ነው።

🟠 ሩሲያ ከአውሮፓ፣ ከእንግሊዝ እና ከአሜሪካ ጋር "በእኩልነት" ለመሥራት ዝግጁ ነች።

ሌሎች

🟠 "ሺ ጂንፒንግን በጣም ጥሩ ጓደኛ እንዲሁም የሩሲያ የታመኑ ወዳጅ እና አጋር አድርጌ እቆጥራለሁ።"

🟠በ"ጊዜ ካፕሱል" ( የሥጦታ ማሸጊያና ማስቀመጫ) መልኩ የቀረበ መልእክት።

🟠"ስለ ምን እያወራ ነው"፤ ማርክ ሩተን አስመልክቶ የተናገሩት።

🟠"እኛ ጭቆናን ወይም የፖለቲካ ስደትን አንፈጽምም።"

🟠"ይህ የእኛ ሚስጥራዊ መሳሪያ ነው፣ ግን የመጨረሻ አማራጭ ሲሆን ብቻ ነው የምንጠቀመው"፣ በታሪክ ውስጥ ከከዋክብት መካከል የመጣ ከፀሐይ ሥርዓት ውጭ ወደ ሥርዓተ-ፀሐይ ሲገባ የተገኘ ሦስተኛው አካል ስለሆነው 3I/ATLAS የሚነሱ የሴራ ትንታኔዎች ላይ የተናገሩት ቀልድ

🟠 "በሞስኮ ውስጥ በድብቅ እነዳለሁ፣ ግን አልፎ አልፎ።"

🟠 "ፍቅር ይዞዎታል? — አዎ!"

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0